ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተመልሰው በባሕር ዳር የሚገኙ ተማሪዎች ከፖሊስ ጋር ተጋጩ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/170960

ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ከሞት አምልጠው ባህርዳር በመድረስ ድምፃቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማሰማት በወጡ ተማሪዎች ላይ የክልሉ አድማ ብተና ድብደባ መፈፀሙ ተነገረ።

ከቀናት በፊት በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ዘርን መሠረት ባደረገ ጥቃት ከሞት አምልጠው ባህርዳር የደረሱት የአማራ ተማሪዎች እስካሁን ችግራቸውን የጠየቃቸው ባለስልጣን አለመኖሩን ተናግረዋል።
ይኸንን ተከትሎም ድምፃቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማሰማት በወጡ ተማሪዎች ላይ የአማራ ክልል አድማ ብተና ድብደባ ማድረሱን ተማሪዎቹ ተናግረዋል።
ጊዎርጊስ አካባቢ ድምፃቸውን በማሰማት ላይ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በክልሉ አድማ ብተና በተፈፀመ ድብደባ 8 ልጆች መጎዳታቸውንም ተማሪዎቹ ተናግረዋል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.