ከእስታይሽ ወደ ወልድያ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተገልብጦ 9 ሰዎች ሞቱ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8A%A8%E1%8A%A5%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%AD%E1%88%BD-%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8B%88%E1%88%8D%E1%8B%B5%E1%8B%AB-%E1%88%B2%E1%8C%93%E1%8B%9D-%E1%8B%A8%E1%8A%90%E1%89%A0%E1%88%A8-%E1%8B%A8%E1%88%85/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ከእስታይሽ ወደ ወልድያ መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተገልብጦ 9 ሰዎች ሞቱ።

አደጋው ዛሬ ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ ተሽከርካሪው መንገድ ስቶ ገደል ውስጥ በመግባቱ መድረሱን የጉባ ላፍቶ ወረዳ ፖሊሲ መምሪያ ሁለገብ የወንጀል ምርመራ ኦፊሰር ዋና ሳጅን ትዕግስት ተናግረዋል።

ተሽከርካሪው በወረዳው 015 ቀበሌ ደቦት በተሰኘ ቦታ ላይ መንገድ ስቶ በግምት 20 ሜትር ጥልቀት ባለው ገደል ውስጥ መግባቱንም ነው የተናገሩት።

በአደጋው እስካሁን የ9 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን አሽከርካሪውን ጨምሮ በዘጠኝ ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ ጉዳት መድረሱንም ጠቅሰዋል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ሲሆን፥ ጉዳት የደረሰባቸው መንገደኞች በወልድያ ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል ብለዋል።

 

በምንይችል አዘዘው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.