“ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት ላለመቅረብ ወስኛለሁ!…” (ኤርሚያስ አመልጋ – ከቂሊንጦ)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/191983

“ከዚህ በኋላ ፍ/ ቤት ላለመቅረብ ወስኛለሁ!…” (ኤርሚያስ አመልጋ – ከቂሊንጦ)
. ድፍን አንድ አመት!… በህግ ሊያስጠይቀኝ የሚችል ምንም አይነት የወንጀል ድርጊት ባልፈጸምኩበት እና ለክስ የሚያበቃ ምንም ተጨባጭ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ለእስር ከተዳረግኩና ፍትህ አገኝ ብዬ ፍርድ ቤት መመላለስ ከጀመርኩ እነሆ ድፍን አንድ አመት ሞላኝ፡፡ የፌዴራል ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤት በአንድ ሳምባ በሚተነፍሱበት ስርዓት እና አገር ላይ፣ ገለልተኛ ፍርድ እና ሚዛናዊ ፍትህ ማግኘት እንደማይቻል በአንድ አመት የእስር ቤት ቆይታዬ ያረጋገጥኩት ሃቅ ነው!!!
ከዚህ በኋላ ፍትህ አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ራስን ማጃጃል አንደሆነ ተገልጾልኛል፤ አሁን ከስርዓቱ ፍትህ የምጠብቅበት ሳይሆን በእኔ ከደረሰውና ዙሪያዬን ከማየው ተነስቼ የአገራችንን የፍትህ ስርዓት ነውረኛ ባህሪ ለህዝብ የምገልጽበት ወቅት ነው፡፡ “መርምረን እናስራለን እንጂ፣ አስረን አንመረምርም” የተባለለትን የለውጥ ዲስኩርና ፕሮፖጋንዳ ተከትሎ፣ ብዙ ተስፋ የተጣለበት የፍትህ ስርዓት፣ ዛሬም እንደ ትናንቱ ፍጹም የመንግስት ወገንተኝነቱን እና የአምባገነን መንግስት መሣሪያና መጠቀሚያ ሆኖ መቀጠሉን ለመላው ኢትዮጵያውያንና ለዓለም በድፍረት ማሳወቅ አስፈላጊ መሆኑን ከልብ አምኜበታለሁ፡፡ ከዜጎች ጎን ሆኖ ለእውነት፣ ለፍትህና ለህግ ልዕልና የሚቆም ስርዓት መገንባት ቀጣይ የአገራችን ዜጎች ትልቅ የቤት ስራ መሆኑን በአጽንኦት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡
ራሳቸውን ከወገንተኝነት ካላጸዱ የፖሊስ፣ የአቃቤ ህግ እና የፍርድ ቤት ተቋማት ጋራ የተጓዝኩበት ረጅም ጎዳና፣ በፍትህ ስርዓቱ ላይ እምነት መጣሌን ትቼ ከመንገዱ ወጣ እንድልና ራሴን በጽሞና እንድጠይቅ አስገድዶኛል፤ አልፎ ተርፎም ከበስተጀርባ በስውር እጆች እየተቀነባበረ የሚሰራብኝ ትልቅ ድራማ እንዳለ ግልጽ አድርጎልኛል፡፡ ከዚህ ቀደም

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.