ከገዥዎቹ ያልተናነሱ ሁለት ክፉዎች! (ከጌታቸው ሽፈራው)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/72604

ከገዥዎቹ ያልተናነሱ ሁለት ክፉዎች! (ከጌታቸው ሽፈራው)
1ኛው:_ በማንነታቸው ምክንያት ብዙዎች የከፋ በደል ሲደርስባቸው ቆይቷል። አማራ በመሆናቸው፣ ኦሮሞ በመሆናቸው፣ ጉራጌ በመሆናቸው ሲዘለፉና ሲገረፉ ኖረዋል። ሲዘለፉና ሲገረፉ ማንነታቸው እየተጠራ ነው። ሲሰለቡ፣ ሲኮላሹ ማንነታቸው እየጠራ ነው። ለዚህ ጭካኔ የተመረጡት በማንነታቸው ነው። ይህ ወንጀል በሚዲያ ሲነገር ብዙዎችን በማሳዘኑ አጭበርባሪዎች ገበያ አደረጉት። የተዘለፉትና የተገረፉት ተገደው ሲሆን፣ አጭበርባሪዎቹ ወደው፣ ፈቅደው ያልሆኑትን እንደተደረገባቸው አስመሰሉ። በተበደሉት ቁስል ላይ ነገዱ።
2ኛው:_ ነጋዴዎች በተበደሉት ስም ሲያጭበረብሩ ነጋዴዎቹን ለመቃወምም ይሁን የተበደሉትን ስቃይ ለማራከስ ቀልድ ጀመሩ። “በብሔሬ ምክንያት እንዲህ ሆንኩ!” እያሉ ይቀልዳሉ። አጭበርባሪዎቹን ለመቃወም ቢሆን ባልከፋ። ነገር ግን እነዚህ አሿፊዎች ሰው በብሔሩ እንደማይጠቃ ሁሉ ቀልድ አድርገውታል።በማንነቱ ተፈርጆ እንዳልታረደ፣ እንዳልተኮላሸ፣ እንዳልተዘረፈ፣ እንዳልተገረፈ ገዥዎቹ በማንነት ፈርጀው ሲገዙና ሲያሰቃዩ እንዳልኖሩ የመከረኞችን ቁስል የሚያመረቅዝ ቀልድ በዝቷል።
በደሉን ያደረሱት የለየላቸው አረመኔዎች ናቸው። ከእነሱ የማይተናነሱት ግን አረመኔዎች በወገናቸው ላይ የፈፀሙትን መጠቀሚያ ያደረጉና በወገናቸው ቁስል የሚቀልዱት ናቸው። ሁለቱም ለገዥዎች የማስተባበያ መግለጫ እያወጡላቸው ነው!
ትህነግ/ህወሓት ኢትዮጵያውያንን በማንነታቸው ሲያጠቃ ቆይቷል። አጭበርባሪዎች ከገዥዎች ወገን ሰነባብተው ወደሕዝብ ወገን ለመሆን “በማንነቴ ተጠቃሁ” ስላሉ በማንነታቸው የተጠቁ የሉም ማለት አይደለም። ይህን መካድ ለደፋሪዎቹ የትህነግ ሰዎች ጥብቅና መቆም ነው።
ትህነግ/ህወሓት በማንነት ሲያጠቃ እንዳልነበር ለማስመሰል የሚሞክሩትም ሆነ የሚያጭበረብሩት በዛ ድቅድቅ የጭቆና ወቅት “አላይም አልሰማም” ብለው የራሳቸውን ህይወት ሲመሩ የነበሩ ናቸው። ትናንት ስሰ ጉዳይ ላይ ሲቀልዱ፣ አሊያም ዝምታን መርጠው ቆይተው ዛሬ ሲፈቀድ በድቅድቁ የአገዛዝ ወቅት መስዋዕት የሆኑት ወገኖች ቁስል

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.