ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ድንገተኛ ሞት በስተጀርባ የጠላት እጅ ይኖር ይሆን? አብረን የምናይ ይሆናል!

Source: https://mereja.com/amharic/v2/77566

ጋዜጠኝ ደምስ በለጠ ከመሞቱ ዋዜማ የነበረውን ውሎ አባይ ዘውዱ እንደሚከተለው ዘግቧል
የታህሳስ 12 ቀን ውሏቸውን በተመለከተ ዛሬ ያገኘሁት መረጃ ይህን ይመስላል – (ለምርመራው ከጠቀመ)
1. ረፋድ 4 ስዓት ላይ ፒያሳ ቀጠሮ አለኝ ብለው መነን ት/ቤት አካባቢ ካለው ከእናታቸው ቤት ወጡ፣
2. 4 ስዓት ላይ ከቤት እንደወጡ ከሁለት ጓደኞቻቸው ጋር እዛው መነን አካባቢ ከሰብለ አረጋ ከተባለች ቤተሰባቸው ቤት ቡና ጠጥተው፣ለ30 ደቂቃ ያህል ከቆዩ በኃላ ስልክ ሲደወልላቸው ፒያሳ የማገኘው ሰው ስላለ በኃላ እመጣለሁ ብለው ከሰዎች ተለይተው ሄዱ።(ዘመዳቸው ሰብለ አረጋ ከተናገረችው) (የተደወለላቸውን ስልክ ሳይ ልክ 4 ስዓት ከ28 ደቂቃ ላይ የደወለላቸው ደግሞ አንድ ጓደኛቸው ነው(ስማቸው ይቆየን)።በአካል ያግኛቸው በስልክ ብቻ ገና አልተጣራም።
3. ከቀኑ 6 ስዓት አካባቢ ስደውልላቸው ሩሲያ ኤግዚቪሽን አካባቢ እንደነበሩ ነግረውኛል።ማገኛቸው ሰዎች አሉ ብለውኛል። (ከእህታቸው ልጅ ከህይወት ተፈሪ ንግግር የተገኘ)
4. ከቀኑ 9 ስዓት ተኩል ወደ እናታቸው ቤት ተመለሱ፣ጥሩ የጤንነት ስሜት ላይ አልነበሩም፣የቀረበላቸውን ምግብ ቀማምሰው ነው የተውት፣የድካም ስሜት አለባቸው፣የሆኑትን ነገር ብትጠይቃቸውም ስሜታቸውን አላጋሯቸውም። (እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ ከተናገረችው )
5. በመሀል አቶ ወርቁ (ጓደኛቸው) እና ወ/ሮ እታፈራሁ ካሳ ወደ እናታቸው ቤት በመምጣት ጋዜጠኛ ደምስንና ቤተሰቡን ሲያጫውቱ ቆዩ፣ከተወሰነ ቆይታ በኃላ እህታቸው ወ/ሮ አዜብ በለጠ እና ልጃቸው ህይወት ተፈሪ ለስራ ጉዳይ ከቤት ወጡ።
6. ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ እና ከእናታቸው ጋር እነ ወ/ሮ እታፈራሁና አቶ ወርቁ ሲጫወቱ እስከ 12 ስዓት አካባቢ አብረው ቆይተዋል፣ነገር ግን በመሀል

Share this post

One thought on “ከጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ድንገተኛ ሞት በስተጀርባ የጠላት እጅ ይኖር ይሆን? አብረን የምናይ ይሆናል!

  1. It is very sad we lost this great son of Ethiopia. What is even more sad is that his life is not being celebrated as it should. What is wrong with us?

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.