ከግብፅ ሴራ ጀርባ ያሉ ኃይሎች እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ ተጠየቀ

Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/107121

አዲስ አበባ፡- በአባይ ግድብ ምክንያት ከግብፅ ሴራ ጀርባ በመሆን የሚንቀሳቀሱ የውጪ ሆነ የውስጥ ኃይሎች እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት አሳሰቡ። ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባላት በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል በአካል ቀርበው እንዳመለከቱት፤ በአባይ ጉዳይ አንዳንድ የውጪና የውስጥ ኃይሎች እየሄዱበት ያለው መንገድ ትክክል ያልሆነና በየትኛውም መመዘኛ ያልተገባ ነው። የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር አባል የሆኑት አቶ ደስታ አርቤሎ፣ የሀገር ጉዳይ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸው፤ አንዳንድ የውጪና የውስጥ ኃይሎች አባይን በተመለከተ የሚያራምዱት አቋም ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል። የትናንት ጀግኖች በጦር ሜዳ በብዙ መስዋዕትነት ያቆዩልን ሀገራችን ስትነካ ያማል ያሉት አርበኛው ፣ ይህ ህመም የትኛውንም ዋጋ ለሀገር ለመክፈል አቅም የሚፈጥር

The post ከግብፅ ሴራ ጀርባ ያሉ ኃይሎች እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ ተጠየቀ appeared first on ዘ-ሐበሻ: ZeHabesha Latest Ethiopian News Provider.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.