ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኃይማኖትና ፖለቲካ አጀንዳዎች ማቀንቀኛ ሊሆኑ አይገባም ተባለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/174905

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኃይማኖትና ፖለቲካ አጀንዳዎች ማቀንቀኛ ሊሆኑ አይገባም ሲል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኃይማኖትና ፖለቲካ አጀንዳዎች ማቀንቀኛ ሊሆኑ አይገባም ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
Image may contain: 17 people, people sitting
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብትና ቴክኖሎጅ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በወቅታዊ የዩኒቨርሲቲዎች አለመረጋጋትና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚታየው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መስተጓጎል መንስኤዎችን ከመለየት፣ የቦርዶችና የየተቋማቱ አመራሮች ችግሮችን እየለዩ በወቅቱ ከመፍታትና በሁከቱ ውስጥ ተሳታፊ በነበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየወሰዱ ከመሄድ አኳያ ምን እየተሰራ ነው የሚሉ ጥያቄዎች ከቋሚ ኮሚቴው ተነስተዋል።
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችን በሀገሪቱ ውስጥ ለተዘራው የፖለቲካና የሃይማኖት አሉታዊ ዜና ሰለባዎች መሆናቸውን አንስተው ችግሩን ለመፍታት በትኩረት እየሰራን ነው ብለዋል።
Image may contain: 1 person, indoor
በሀገሪቱ ውስጥ ካሉት 45 ዩኒቨርሲቲዎች በአሁኑ ወቅት ችግሩ የተከሰተባቸው 25 መሆናቸውንና ችግሩን ለመቅረፍ ከፍተኛ ርብርብ በመደረጉ አብዛኞቹ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወደ ሰላማዊ የመማር ማስተማር እንቅስቃሴያቸው ተመልሰዋል ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኃይማኖትና ሌሎች የፖለቲካ አጀንዳዎች ማቀንቀኛ ቦታ መሆን እንደሌለባቸው ቢታመንም የጥፋት አጀንዳ ባላቸው ውጫዊ አካላት ሰለባ መሆናቸውን የተናገሩት ፕሮፌሰር ሂሩት፥ ተቋማቱ ባሉበት አካባቢ የሚገኙ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ጣልቃ ገብነት የከፋ በመሆኑ የመማር ማስተማር ስራቸውን ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ለማከናወን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.