ከ30 በላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ተዘግተዋል – ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቷል።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/154560

ከ30 በላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ተዘግተዋል። በአዲስ አበባ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቷል።መንገድ መዘጋቱ ለመጉላላትና ለችግር ዳርጎናል ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በመስቀል አደባባይ የሚከናወኑ ልዩ ልዩ ስነ-ሥርአቶች ተጀምረው እስከሚጠናቀቁ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ ፖሊስ የራሱን የተለመደ መግለጫ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት፡-
ጎተራ ሼል ዴፖ
ጎፋ ማዞሪያ
ቄራ 6 ቁጥር ማዞሪያ
ሳር ቤቶች
ካርል አደባባይ
 ጦር ኃይሎች አደባባይ
ኮካኮላ ድልድይ
ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
ልደታ ፀበል
አብነት አደባባይ
ሞላ ማሩ መገንጠያ
በርበሬ በረንዳ
ተክለ ሃይማኖት
ቴዎድሮስ አደባባይ
ንግድ ማተሚያ ቤት
አሮጌው ቄራ
ባሻወልዴ
ፓርላማ መብራት
ጥይት ቤት
ጀርመን አደባባይ
ሲግናል
እንግሊዝ ኤምባሲ መገንጠያ
ለም ሆቴል
ሾላ ገበያ መብራት
ጎርጎሪዮስ አደባባይ
መስቀል ፍላወር
መገናኛ ላይና ታች
ኤድናሞል አደባባይ
ሰንሻይን መገንጠያ
ቦሌ ቀለበት እና ቦሌ ሚካኤል ወደ ዝግጅቱ ስፍራ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

Share this post

One thought on “ከ30 በላይ የአዲስ አበባ መንገዶች ተዘግተዋል – ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ተከስቷል።

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.