ካፍ የ2019 ምርጥ ተጫዋችና አሰልጣኝ እጩዎችን ይፋ አደረገ

Source: https://fanabc.com/2019/11/%E1%8A%AB%E1%8D%8D-%E1%8B%A82019-%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%A5-%E1%89%B0%E1%8C%AB%E1%8B%8B%E1%89%BD%E1%8A%93-%E1%8A%A0%E1%88%B0%E1%88%8D%E1%8C%A3%E1%8A%9D-%E1%8A%A5%E1%8C%A9%E1%8B%8E%E1%89%BD%E1%8A%95/

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2019 ምርጥ ተጫዋችና አሰልጣኝ እጩዎችን ይፋ አደረገ።

ከ10 በላይ በሆኑ ዘርፎች ከቀረቡ እጩዎች መካከል አሸናፊው ከአንድ ወር በኋላ በግብጽ በሚካሄድ የሽልማት ስነ ስርዓት ይታወቃል።

በወንድ ተጫዋቾች የቻምፒየንስ ሊግ አሸናፊዎቹ ሞሃመድ ሳላህና ሳዲዮ ማኔን ጨምሮ፥ አልጀሪያውያኑ ሪያድ ማህሬዝ እና ዮሴፍ ቤላይሊ እንዲሁም የአርሰናሉ ኦባሚያንግ ይገኛሉ።

በአሰልጣኞች ዘርፍ ደግሞ የአልጀሪያው ጃመል ቤልማዲ፣ የሴኔጋሉ አሊው ሲሴ፣ የናይጀሪያው ገርነት ሮር እንዲሁም የዛማሌኩ ክርስቲያን ግሮስ ተካተውበታል።

በምርጥ ብሄራዊ ቡድን ዘርፍ ደግሞ አልጀሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ናይጀሪያ፣ ሴኔጋል እና ቱኒዚያ እጩ ሆነዋል።

የሽልማት ዘርፎቹ በወንዶችና በሴቶች ኮከብ ተጫዋችነት፣ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ፣ የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች፣ የአመቱ ምርጥ ቡድን፣ የአመቱ ምርጥ ጎል እና ምርጥ 11ን ያካተተ ነው።

 

 

ምንጭ፦ cafonline.com/

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.