ክብር ስለሚጨፈጨፈው ወገናቸው ለሚቆረቆሩ የአማራ ካህናት!

Source: http://welkait.com/?p=12163
Print Friendly, PDF & Email

 (ከታዘቢ)

የወያኔ ስርአት የአማራ ነው በማለት በአማራ አምሳል አንቋሾ በማቅረብ ለማጥፋት ብዙ ከደከመባቸው መካከል ካህናት ግንባር ቀደም ናቸው። ጥቂት ከስርአቱ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸውንና ወንጀልን ከአለማዊ ሰው በበለጠ የሚፈፅሙ ካህናትን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት አማራ ካህናትን ከስራ መደባቸው አፈናቅሎ ነገር ግን አሁንም በቤተ እመነቱ የሚያገለግሉት ካህናት አማራ እንደሆኑ በማስመሰል የስርአቱ አገልጋይ ተገዳላይ ካህናቱን ሰካራምነት: ውሸታምነት: ሌብነት ለአማራ በመስጠት አማራን ከነእምነቱ ለማራከስ ብዙ ተሰርቷል።

እምነቱ ግን የአማራ ብቻ ሳይሆን እነሱ የፈለቁበትም ህዝብ ነበር። ይሄ ሁሉ አስነዋሪ ተግባር እየተፈፀመባቸው ያሉ የአማራ ካህናት አሁንም ህዝባቸው ጎን ናቸው። በእምነታቸውና በብሄራቸው ምክንያት በየቦታው የአማራ ህዝብ ጋር በጅምላ የተጨፈጨፉትና የተሰደዱትም የአማራ ካህናት ናቸው። የአማራ ህዝብ አባቶች የሆኑት እኝሁ ካህናት ይሄን ሁሉ መከራ ከህዝባቸው ጋር እየተቀበሉ በአባትነታቸው ደግሞ ተማርን እንደምንለው እንደኛ አንድ ጊዜ በአንድነት ስም ሌላ ጊዜ የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ በሚል ምክንያት ወገናቸው ላይ የሚፈፀመውን ግፍ ከዳር ቆመው አይመለከቱም ይልቁንም እየተጨፈጨፈ ካለው ወገናቸው ጎን በመንፈስ ብቻ ሳይሆን በአካልም ሄደው ይቆማሉ።

ዛሬ ያገኘኃቸው ሁለት ካህናት ለዚህ ምሳሌ ናቸው። በአዲስ አበባ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት እነዚህ ሁለት አማራ ካህናት የወልድያውን ጭፍጨፋ እነደሰሙ በህዝባቸው ጨክኖ ዝም ማለት አልተቻላቸውም። ጭፍጨፋው በተፈፀመ በሶስተኛው ቀን ለህይወታቸው ሳይሳሱ ሀዘን ላይ ወደሚገኘው ወገናቸው በመሄድ የደረሱበትን ቀብረው: ሀዘን ላይ የተቀመጡትን አስተዛዝነው: መስዋዕት ለሆኑ ለወገኖቻቸው ፀልየው በወቅቱ ከወልድያ በቀጥታ በደሴ በኩል ወደ አዲስ አበባ መምጣት ስላልቻሉ በጎንደር መስመር እስከ ኮን ሄደው በዋድላ በኩል ነው አዲስ አበባ የገቡት። ይሄን ሁሉ ያደረጉት እኛ በአንድነት ስም ታጅለን ለተውነው አማራ ወገናቸው ነው።

እኛ ለመሄድ አስበን በማሰባችን ብቻ ሌላ ነገር ያመጣብን ይሆን ብለን በምንጨነቅበት ሁኔታ ነው እነዚህ የአማራ ህዝብ አባቶች የወንድሞቻቸውና የልጆቻቸው ደም የፈሰሰበት ጎዳና ሳይደርቅ ከህዝባቸው ጎን የቆሙት! እኔ ታዳሚ በነበርኩበት ቤተ ማህበር ሲያስተምሩ “ሁላችንም ችግር ውስጥ ነው ያለነው! ዛሬ በወንድሞቻችን ቤት የደረስ ሁሉ ነገ በሁላችን ቤት ይገባል! አሁን ነው አብረን መቆም ያለብን!”

“አንድ አማራ ለሁሉም አማራ! ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!” ማለት ይሄው ነው: አማራው ካህን አባታችን የተናገሩት።
# ክብር በመከራ ጊዜ ከወገናቸው ጎን ለሚቆሙ ካህናት አባቶቻችን!

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.