ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

Source: http://amharic.ethsat.com/%E1%8A%AE%E1%88%88%E1%8A%94%E1%88%8D-%E1%8C%8B%E1%8B%B2%E1%88%B3-%E1%8C%89%E1%88%9B-%E1%8A%A8%E1%8B%9A%E1%88%85-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%88%9D-%E1%89%A0%E1%88%9E%E1%89%B5-%E1%89%B0%E1%88%88/

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 24/2010)የመጀመሪያውን የአየር ሃይል አውሮፕላንን ከሲውዲን ወደ ኢትዮጵያ ከሌሎች ሶስት ኢትዮጵያውያን ጋር እያበረሩ የገቡት ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

በተለያዩ አለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ የበረራ ትምህርትን የተከታተሉትና የመጀመሪያ የአብራሪ ክንፍ ያገኙት ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ የክብር ተሸላሚም ነበሩ።

35 አመታትን በአየር ሃይል ውስጥ ያገለገሉት ኮለኔል ጋዲሳ በክብር በጡረታ ከተሸኙ በኋላ በሌላ ዘርፍ ሀገሬን ላገልግል በማለት በተለያዩ የአለም ሀገራት ሲዘዋወሩ የተመለከቱትን የሆቴል ስራ በዘመናዊ መልክ በሀገራቸው ለመገንባት በማቀድ መስቀል ፍላወር ሆቴልን በአዲስ አበባ ከፍተዋል።

በሆቴል ስራ ለአንድ ካገለገሉ በኋላ የደርግ መንግስት ሲወድቅ ለ8 አመታት በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደርገዋል።

ሀገራቸውን በቅንነት ያገለገሉት ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ የአሁኑ ስርአት ባሳደረባቸው ጫና ለስደት ተዳርገው ኑሮአቸውን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ አድርገው ነበር።

ኮለኔል ጋዲሳ ጉማ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ96 አመታቸው በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 28/2017 ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነስርአታቸውም ቅዳሜ ህዳር 4/2017 በኦክላንድ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ይፈጸማል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.