ወያኔ በማማለል ኢትዮጵያን የሚገዛበት እድሜ አብቅቶለታል! (ሥዩም ወርቅነህ)

Source: http://ethioforum.org/amharic/%E1%8B%88%E1%8B%AB%E1%8A%94-%E1%89%A0%E1%88%9B%E1%88%9B%E1%88%88%E1%88%8D-%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8C%88%E1%8B%9B%E1%89%A0%E1%89%B5-%E1%8A%A5/

የወያኔ ቃላቀባይ ልማታዊ ጋዜጠኛው ዳኔል ብርሃኔ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተመርጧል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ሆኗል ይለናል። በነገራችን ላይ ደመቀ መኮንን ሲገልጠው “The first muslim Prime Minister”…

Share this post

One thought on “ወያኔ በማማለል ኢትዮጵያን የሚገዛበት እድሜ አብቅቶለታል! (ሥዩም ወርቅነህ)

 1. “ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን “The first muslim Prime Minister”…ተመርጧል
  አቶ ሺፈራው ሽጉጤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ ተመርጧል ይላል።”(የወያኔ ቃላቀባይ ልማታዊ ጋዜጠኛው ዳኔል ብርሃኔ)
  ” ሕወሓት አንድ አጋስስ በሶስት ምክትል አጋስሶች በሰባት ጫኝና አውራጅ ስድስት ዓመት ተደናብሮ ያልቻለውን አሁን አንድ አህያና አንድ በቅሎ ቢመርጥ ምን ይመጣል!? በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ ሕዝቡ እንደሆን ብሏል ይለያል ዘንድሮ። የሆነው ሆነና ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ባለፈው ያሳየው አስደማሚ የጨዋ የመብት ጥያቄ ሰልፍ ሙስሊም ጠ/ሚኒ እንዲመረጥለት ነበር? ከጭፈራ ውጭ ምንም ያልተጠቀመ ይልቁንም የታገተው የደቡብ ሕዝብ ዳግም እንዲታፈን ሺህፈራውን ማንገስ?
  ** ኢትዮጵያ በዘርና ቋንቋ ልዩነት እርስ በእርሱ ማባላት ፵፫ ዓመት ተወጥኖ ያቃታቸውን፡ አንድነት ኅይል ነው ብሎ የተነሳን ሕዝብ አሁን በሃይማኖት ገብቶ ለማበጣበጥ አጀንዳ ቀረጻ ካልሆነ የሕዝብ ጥያቄ ፍትህ፡እኩልነት፡ሰላም፡ ሥራ፡ትምህርት፡ ጤና፡ በነጻነት መናገር መጻፍ መጠየቅ ፈጣን ምላሽ ማግኘት፡ ተዘዋወሮ በፈለገው አካባቢ እንዲሰራ በጎጥና ነገድ ተመትሮ ሳይሆን በዜግነቱ ተከብሮ መኖር እንጂ አፈ ቅቤ ሆደ ጩቤ ከርሳም አፈላልጎ ለፎቶ ማቅረብ በሕዝብ መሳለቅ ነው። ይልቁንም አመጽና ተቃወሞውን ማባባስ ፈጣኑን አዋጅ ዘገምተኛ ማድረግ ጥሩ ስልት እንዲሆን ታስቦ ነው።
  ሕዝብ ጥያቄ ሥርዓቱ አብሮ ሊያኖር ብቻ ሳይሆን አብሮ ኳስ አላጫወተም ፡ ጎጠኝነት ለሀገር ሉዓላዊነት ፀር፡ ክልል ለሀብት ክፍፍል ሳይሆን የሙሰኞች መፈለፈያ ወታቦ ሆኗል፡ አብዮትና ዲሞክራሲ ተሳከረዋል እያለ ነው። ይህን ለማረቅ ግን ጴንጤውን ብሙስሊም ከንባታውን በወሎዬ ሳይሆን ፍረሃ እግዝሐብሔር ባላቸው፡ ቅን አሳቢ ሀገራዊ ተቋሞችን መገንባት በሚችሉ ምሁራን መቀየሩ የተሻለ ነው። አለዚያ አንካሳን በሸፋፋ…ጎባጣን በጠማማ ሆነ በለው!

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.