ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ እየጋገረ ነው ፤ አራተኛው ምዕራፍ

Source: http://amharic.abbaymedia.com/archives/29694

ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ እየጋገረ ነው ፤ አራተኛው ምዕራፍ!

በመስቀሉ አየለ
የወያኔን እራሱን እንደ ዳይኖስረስ የመብላት ሂደት መዘገብ ከጀመርኩበት ግዜ ጀምሮ ባጭሩ ሲጠቃለል በሳሞራ የሚመራው የወታደሩ ክንፍም ይሁን በጌታቸው የሚመራው የደህንነቱ ክንፍ ሁሉም በየፊናቸው የመንግስትን ስልጣን ለመቆጣጠር በሚያደርጉት ግብግብ በክልልና በወረዳ ደረጃ ያላቸውን መሰረት በማጠናከርና ከማእከላዊ መንግስቱ ገንጥሎ በማዳከም ብሎም የራሳቸው አሻንጉሊት በማድረግ አይናቸውን በማእከላዊ መንግስቱ ላይ ማፍጠጣቸውን፤ ይኽም የመጨርሻው ምእራፍ መቃረቡን እንደሚያሳይ ገልጠን ወደ ወሳኙ ምእራፍ ለመሸጋገር ግን ሁለቱም በየፊናቸው ከተጻራሪ ወገን ጀርባ ያለውን የፖለቲካውን ድጋፍ ሰጭ ሃይል በመምታት ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ገልጨ ነበር የቋጨሁት፤ መሰረቱን በዋሽንግተንና በአምስተርዳም ባደረገው ኢሳት ቴሌቪዥን ባለፈው የተገለጠውና አንጃዎቹ መሃል የተፈጠረውን ቅራኔ በገለልተኛ ሽማግሌዎች ለመፍታት እየተደረገ ነው የተባለው ጥረት እውነተኛ መሆኑን እኔም በሌላ ምንጭ የማውቀው መሆኑን አረጋግጣለሁ፤ ይልቁንም መረጃው ወደ ህዝብ ጆሮ መድረሱ በሽምግልናው ሂደት ላይ ከባድ ቀውስ ማስከተሉን ወትሮም በቋፍ የነበረውን ሂደት ከድጡ ወደ ማጡ እንዳደረገው እየታየ ነው።

እዚህ ላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ማወቅ ያለበት ቁልፍ ነጥብ ወያኔ ባለፈው አራት አስርተ አመታት የመጣበት የውስጥ ቀውሱን ይፈታባቸው የነበሩት “ግምገማ፣ግለሂስና” ተሃድሶ የሚባሉት ሶስት ነባር ልምዶቹ የራሳቸውን ሂደት ጨርሰው የነፈሰባቸው (ፌዝ አውት) ያደረጉ መድሃኒቶች መሆናቸውንና ይኽ ነው የሚባል የችግሩን ውስብስብነትና የአደጋውን ጥልቀት የሚመጥን ሌላ አማራጭ መፍቻ መንገድ ያልተገኘ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ሊገኝ የማይችል በመሆኑም ጭምር ነው ወደ ሽማግሌዎች ትከሻ ላይ ለመጫን የተገደዱት ፤ ይሕ የትግራይ ገዥ ጉጅሌ በዘር ተደራጅቶ የፈጸመው ስንት ውስብስብ ብሄራዊ ወጀል እንደ መኖሩና ከላይ እስከ ታች ያሉት ባለስልጣናት በግል የገቡበት ስር የሰደደ የዘረፋ ወንጀል ሁሉ የነሱን ዘር በማይወክሉ ሃይሌ ገብረስላሴና ፕሮፌሰር ይሳሃቅ ኤፍሬምን የመሳሰሉ የሰውነት ወዝ የሌላቸው ድኩማኖች ሽማግሌ አድርገው ለማየት ስብሰባ ሲቀምጡ የቱን ሚስጥር ተናግረው የቱን መደበቅ በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ከሚደረግ ሽምግልና የሚገኝ ውጤት ሂደቱን ሳይወለድ የጨነገፈ አድርጎታል።

በእርግጥም ወያኔ ደጋፊዎቹ እንዲህ እያወቁለት ያለ ባህሪው ያውም ለራሱ ከሚሰማው እብሪት አንጻር በጣም በሚንቃቸው ሰዎች ፊት “ገመናዬን ለማቅረብ ዝግጁ ነኛ” ማለቱ በጣም አሳፋሪው የቁም ሞቱ ነው።
በሶስተኛው ምዕራፍ ላይ የነበረውን የሃይል አሰላለፍ ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ እንዲሸጋገር ካደረጉት ምክኛቶች አንዱ እስካሁን በነበረው አሰላለፍ ገለልተኛ ሆኖ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቶ የሰነበተው ኃይለማርያም ደሳለኝ “መሃል ሰፋሪ በሁለት ጥይት ይመታል” እንዲሉ ከሁለት በኩል በረዶ ሲወርድበት ከርሞ እርሱ የሚመራውን የደቡብን ክልል ከነግሳንግሱ ይዞ ወደ ሳሞራ ክንፍ መግባቱ ነው፤ አንድ አመት ሙሉ ተጠና ስለተባለው የሙስና እና የጥልቅ ተሃድሶ ዶሴ በተመለከተ “የማውቀው ነገር የለም” በማለት ውሃ ያፈሰሰበትና የፈሪ ዱላ የሚመስል ነገር ለመወርወር የሞከረው “ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ከውጭ ታሳድራለች” አይነት መሆኑ ነው።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያን ቴሌቪዥንና ሬዲዮ የተቆጣጠረው ጌታቸው አሰፋ ኦሮሚያን በተመለከተ እርሱ የማይፈልገው ምንም አይነት ፕሮግራም እንዳይተላለፍ አደረገብን በሚል ችግሩ በጥርስ አልባው ፓርላማ ቀርቦ ተጣርቶ እንዲቀርብ የሚል ውሳኔ ሲወሰንበት የታየበት ድራማ ሁሉ በዚሁ ኦሮሚያ ለሳሞራ የኑስ በመገበሩ የተነሳ የመጣ ችግር መሆኑ ነው።
የጌታቸው አሰፋን ክንፍ በተመለከተ “ጀነራል” ሰዓርን በሳሞራ ምትክ የኢታምሃዦር ሹም ለማድረግ ቢያስችለኝ በሚል በጀነራሎቹ መሃል የሃይል ክፍፍል እንዲፈጠር ለማድረግ እየሰራ ሲሆን ሳሞራ በበኩል አይታመኑልኝም የሚላቸውን እና ቁርጠኝነት የማያሳዩ ናቸው ያላቸውን ጀነራሎች ሁሉ ከፊት በማጽዳትና ታማኝ ሎሌዎችን በመሾም ላይ ተጠምዷል።

ሁሉ ቦታ አለሁ የማለት ጠባይ ያለውና ቀርበው ሲያዩት ከዲንጋይ የተጠረበና ህይወት አልባ የሚመስለው አረመኔው ደብረጽዮን ለግዜው አድፍጦ የሚሆነውን ከቅርብ እርቀት መከታተሉን የመረጠ ሲሆን ባልተጠበቀ ሁኔታ አርከበ እቁባይ ከዚህ የሃይል ክፍፍል በማፈንገጥና ሶስተኛ ክንፍ በመፍጠር ከተቻለ እራሱን ቀጣዩ ጠቅላይ ሚንስቴር ካልሆነም ከአንድ አሻንጉሊት ጠቅላይ ሚንስቴር ጀርባ ተቀምጦ ሁሉንም የሚዘውር “ኪንግ ሜከር” ለመሆን እየሞከረ ሲሆን የተቻለውን ያህል የህወሃት የመጨረሻው እርከን ድረስ በመውረድ የውስጥ ለውስጥ የፕሮፓጋንዳ ስራ በመስራትና ደጋፊ በማሰባሰብ ላይ ትኩረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ነው።

በሃይል አሰላለፉ ውስጥ የታየው ሌላው ለውጥ የውጭ መንግስታት አቋም እስከዛሬ ድረስ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ለነጌታቸው አሰፋ አንጃ አንጻራዊ ወገንተኝነት አሳይተው የነበሩት የምዕራባውያን መንግስትታ ሁኔታውን በጥልቀት በመገምገም የአቁዋም ለውጥ አሳይተዋል፤ ይኸውም ኮማንድ ፖስቱ ቃል በገባው መሰረት ችግሩን በመጀመሪያ ስድስት ወር ውስጥ መፍታት አለመቻሉ እንዲሁም እንደ ቀላል በኦሮሚያ የተጀመረው የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ምክንያት አድርጎ በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት በሂደት ወደ ሰሜን መዛመቱ ብቻ ሳይሆን የትግሉ ባህሪ ወደ ነፍጥ ደረጃ ያደገና መሆኑ በዚህ እኩይ ስርዓት ተስፋ እንዲቆርጡ አድርጓቸዋል።

ዛሬ ለነሱ ማለት ወያኔ ማለት እንኩዋን የተነሳውን ችግር የመፍታት አቅም ሊኖረው ጭራሽ በራሱ ውስጥ ያለው ቅራኔ እንኩዋን አስታርቆ ወደ ፊት ለመሄድ ተስኖት እንዲህ ሲልፈሰፈስ ማየታቸውና ብሎም አቸናፊ ሆኖ ሊወጣ የሚችለውን አካል በቀላሉ መለየት የማይቻልበትን ሁኔታ ሲያዩ አይናቸውን ከወያኔ በመንቀል ሌላ ማረፊያ ቢፈልጉ የሚገርም አይደለም።ወያኔም ቢሆን በዲምፕሎማሲው ዘርፍ ጸሃይዋ እንደ ጠለቀችበት በደንብ አውቆታል። በዚሁም የተነሳ ምዕራባውያን ከዚህ በፊት ባልታዬ ስጋት በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ዳይናሚክስና ተጽእኖ ፈጣሪ ያሏቸውን ግለሰቦች እየመረጡ በሚስጥር በር ማንኳኳትና መምከር ከጀመሩ ሰነባብተዋል።-

Share this post

One thought on “ወያኔ የመጨረሻውን እርሾ እየጋገረ ነው ፤ አራተኛው ምዕራፍ

  1. abiyotawi democracy · Edit

    Lam alegn besemay wotetuanem ale timketegna amahara. Yewore demamitken much beleh agenda. Goteh deress bemegebat ameberkeken yemenegeza egna tigrioch men nefetam nefetegna.

    Reply

Post Comment