ወደ ኢትዮጵያ እመጣለሁ በመንግሥት ደረጃ ተጋብዣለሁ። – ተስፋዬ ገብረአብ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/139269

BBC Amharic
ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ ስቶክሆልም እያለ ነበር ያነጋገርነው። ስቶክሆልም የተገኘው አዲሱ መጽሐፉን [የቲራቮሎ ዋሻ] ለማስተዋወቅ እንደሆነ ነግሮናል። ይህ አዲሱ ሥራው ዘጠነኛ መጽሐፉ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሳተማቸው መጽሐፍቶቹ የተነሳ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ አንባቢያን ስሙን ያነሱታል፤ ይጥሉታል። እርሱም ይህንን ያውቀዋል።
ስንት ዓመት ሆነህ?
እድሜዬ ማለትህ ነው?
አዎ
ልክ 50፤
አረጀህ?
አዎ እያረጀሁ ነው። ለመሞት 50 ዓመት ብቻ ነው የቀረኝ [ሳቅ]
ከሀገር ከወጣህ ትንሽ ረዘም ያለ ጊዜ ስለሆነህ ከአዲስ አበባ፣ ከኢትዮጵያ ምንድን ነው የሚናፍቅህ?
የሚናፍቀኝ አንድ ነገር ብቻ ነው። ቢሾፍቱ ሐይቅ፤ ሆራ፣ የአድዓ መልከዓ ምድር፣ ባቦ ጋያና ጋራ ቦሩ የተባሉ በልጅነት የሮጥኩባቸው መስኮች፣ ሐይቆች፤ እነ በልበላ ወንዝ፣ እነዚህን ድጋሚ ማየት ይናፍቀኛል።
በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ትመጣለህ ተብሎ በሰፊው ሲወራ ነበር፤ ቀረህ?
አይ አልቀረሁም። አልሟላ እያለኝ ዘገየ እንጂ አልቀረሁም፤ እመጣለሁ። በመንግሥት ደረጃም ተጋብዣለሁ። ስላልሞላልኝ ነው እስካሁን ያልመጣሁት።

ስለዚህ ቲኬትም ቀንም አልቆረጥክም ማለት ነው?
ቀንም አልቆረጥኩም፤ ቲኬትም አልቆረጥኩም። ባለፈው ግን ወደ ስቶክሆልም ስሄድ በአዲስ አበባ በኩል አልፌያለሁ።
የአማርኛ ሥነጽሑፍን የሚያጠኑ ሰዎች በሥራዎችህ የት ስፍራ ላይ እንዲመድቡህ ነው የምትፈልገው? ከነ በዓሉ . . .
እንደዚህ አይነት ነገር አስቤ አላውቅም። መጻፍ እወዳለሁ፤ ያመንኩበትን ነገር እጽፋለሁ። ሰዎች ቢወዱትም ባይወዱትም በፍፁም አስጨንቆኝ አያውቅም። ካልወደዱትና ከወረወሩት የሰዎቹ ፈንታ ነው። እኔ ማድረግ ያለብኝ ጥሪዬን መከተል ብቻ ነው ብዬ ነው የማስበው።
አንባቢዎች አልወደድነውም ያሉህ ሥራ አለህ?
ሥራዎቼን በጣም የሚወዱትና በጣም የሚጠሉት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.