ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደረገው በረራ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል ተባለ

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%8B%88%E1%8B%B0-%E1%8A%A4%E1%88%AD%E1%89%B5%E1%88%AB-%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%88%98%E1%88%AB-%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%A8%E1%8C%88%E1%8B%8D-%E1%89%A0%E1%88%A8%E1%88%AB-%E1%89%A0/

(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 4/2010) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደርገውን በረራ በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ እንደሚጀምር አስታወቀ።

ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ እንዲሁም ከአስመራ ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ መንገደኞች ያለ ቪዛ በፓስፖርት ብቻ መጓዝ እንደሚችሉም ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻንም ወደ 114 ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።

ወደ አስመራ የሚደረገው በረራም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ማክሰኞ ሐምሌ 10/2010 በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚጀምርም ተመልክቷል።

አንድ ሰአት ከ10 ደቂቃ በሚፈጀው በረራ የሚጓዙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን መንገደኞች ፓስፖርት እንጂ ቪዛ እንደማይጠየቁም ተገልጿል።

ቪዛው መዳረሻቸው ወደ ሆነው አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ እንደሚመታላቸውም ተመልክቷል።

 

The post ወደ ኤርትራ አስመራ የሚያደረገው በረራ በቀጣዩ ሳምንት ይጀመራል ተባለ appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.