ወዴት እየሄድን ነው? ከባይሳ ዋቅ-ወያ (ለውይይት መነሻ) – ባይሳ ዋቅ-ወያ

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81471

ሰሞኑን ካገር ቤት የሚደርሰው ዜና እንደሁ “ያለ ወትሮው” ቸር ወሬ ላለመሆን የወሰነ ይመስላል። ባለፈው ሳምንት ሁለት ጄኔራሎች ከዱ ብለውን ”በመገረም“ ላይ እያለን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩን አጅቦ ለተመድ ስብሰባ ወደ ኒውዮርክ ሄዶ የነበረው ታዋቂው የልፍኝ አስከልካይ አሜሪካን አገር ጥገኝነት ጠየቀ ሲሉን “ዕጢያችን ዱብ ብሎ” ነበር። ዛሬ ደግሞ ማምሻው ላይ አቶ አባዱላ ገመዳ የአፈጉባዔነት […]

Share this post

One thought on “ወዴት እየሄድን ነው? ከባይሳ ዋቅ-ወያ (ለውይይት መነሻ) – ባይሳ ዋቅ-ወያ

 1. ….አንቀጽ ፴፱ ወጥመድ ነው። ለመገንጠል ምክንያቴ “እኔ እናንተን አልመስልም” ብለህ ማመን አለብህ። እንግዲህ እናንተን አልመስልም ስትል፡ መጤ፡ ሰፋሪ፡ ተስፋፊ/ወራሪ ሆነህ እራስክን በራስህ ማንነትህን ጥለህ ለአፋልጉኝ እንድታለቅስ ያደርግሃል።ከማይመስሉህ ጋር ሜንጫ ትማዘዛልህ! *ከዚያ በኋላ ብሔር፫ ብሔረሰቦች፪ እና ሕዝቦች፩ በእኛ የተፈጠሩ፡ ለእኛ የሚኖሩ፡ ያለእኛ የሚበታተኑና የሚጠፉ ሲባል ቋንቋን ለፈጠረልኝ ፈጣሪዬ ህወሓ ተመስገን ትላለህ። “አዲሲቷ ኢትዮጵያ ፻ ዓመት ኖራ ፳፮ ዓመት እንዲህ ታለፈ..መግንጠል ስትጠይቅ ለማስተደዳደር የያዝከውን መሬት ለባለቤቶቹ ትመልሳልህ። አለበለዚያ የኢንዲስትሪ መር ኢኮኖሚ ግንባታና እስታዲየም ከቢራ ፋብሪካ ጋር የተገነባላቸው የድሮው አይመልስም ሲሉ የዛሬውን አስረክበው እንዲህ የጎጥና ቋንቋ ፌደራሊዝሙና ሕገመንግስቱ እንዲቀጥል እንቅልፍ አጥተው ያድራሉ።
  youtube.com/watch?v=GKJtrXZhJvw
  (ስናፍቅሽ)
  “የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኖ 400 ተማሪዎች ኢትዮጵያዊ አይደለሁም በማለታቸው እንዳልተመደቡ ሰማን፡፡ እንግዲህ አስራ ሁለት ዓመት የደከመ ተማሪ እንዲህ ያለውን ቅጽ ሲሞላ የሚመጣበትን በደንብ የሚያጤነው ይመስለኛል፡፡ ግን አልፈራም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ብሔሩ ከዜግነቱ በላይ እንዲደምቅ ሲነገረው ያደገ አዲሱ ትውልድ ነው፡፡መንገዱን የት ድረስ እንደምንሄድበት ማሳያ ይመስለኛል፡፡ርቀቱንም ጥልቀቱንም ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ አጋጣሚ ነው፡፡ ፬፻ ተማሪ መንግስት ፲፪ዓመት ኢንቨስት አድርጎበት ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ስላለ በምደባው አልተካተተም ብሎናል፡፡ይሄም ቢሆን ግን ተጠያቂ የሚያደርግ ይመስለኛል፡፡
  ኢትዮጵያዊ ያልሆነን ሰው ፲፪ዓመት አንድ ዜጋ የሚያገኘውን ጥቅም በመስጠት አስተምሮ አሁን ማግለል አይቻልም!፡፡ኢትዮጵያዊ አይደለንም ቢሉ እንኳን ያጭበረበሩ የውጪ ዜጎች ተብሎ ክስ መክፈት አሊያም ልጆች ሆነው የተሳሳቱ ተብሎ የዜግነት ትምህርት(ታደሶ) ያሰጣል ብዬ አስባለሁ፡፡ ከትርኢቱ የምንማረው ነገር ግን አለ፡፡…(!?)”
  ______________________!
  ….አንቀጽ 2 የኢትዮጵያ ግዛት የፌዴራል አባላቱን ወሰን የሚያጠቃልል መሆኑን ሲያሳውቅ፣ አንቀጽ 40 (3) “ . . . መሬት…የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ንብረት ነው” ብሎ ያውጃል፡፡ ሕጉ ይህንን ቢልም መሬትን የየክልልና የየብሔር ብሔረሰብ ንብረት አድርጎ የቆጠረ ብሔረተኛ አስተሳሰብ ሕዝብ ውስጥና መንግሥታዊ አስተዳደር ውስጥ ሲያሳስትና ጥፋት ሲያሠራ እናገኛለን፡፡

  አንቀጽ ፰(፩) “የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች፣ የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች ናቸው” ሲልም በማያሻማ ሁኔታ የአገሪቱ ሥልጣን አዛዥነት የፕሬዘዳንት ወይም የጠቅላይ ሚኒስትር ሳይሆን የእነሱ መሆኑን የሚናገር ነው፡፡ አዛዥነታቸው(የሥልጣን ባለቤትነታቸው)የሚገለጸውም በተወካዮቻቸውና በቀጥተኛ ውሳኔያቸው አማካይነት ነው(አንቀጽ ፰፡፫)፡፡ እነዚህ ንዑስ አንቀጾች በብሔረተኛ አዕምሮ ውስጥ ውላቸውን ስተው ልክ እያንዳንዱ ብሔር ብሔረሰብ ሉዓላዊ ህልውና ያለው ተደርጎ ይታሰባል፡፡

  በአንቀጽ ፰(፩) ንዑስ አንቀጽ የአማርኛ ቅጂ ውስጥ ያለው “የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን” በእንግሊዝኛው “”Ethiopia’s Sovereign Power/Ethiopian State Sovereignity” በሚል ዓይነት አገላለጽ በመቀመጥ ፈንታ፣ “All Sovereign Power” ተብሎ መቀመጡ ለአሳቻ ትርጉም ሳያመች አልቀረም ሊባል ቢችልም፣ የአማርኛው ቅጂ ውስጥ ቁልጭ ብሎ የተቀመጠውን እሳቤ የተረዳና በአንቀጽ ፻፮ ላይ የሠፈረውን የመጨረሻ ሕጋዊ ዕውቅናን ለአማርኛው ቅጂ የሰጠ ድንጋጌ ያስተዋለ ሰው መምታታት አይደርስበትም!!፡፡ እውነቱን ለመናገርም የአሳቻ ግንዛቤው ምንጭ ከአንቀጹ ይልቅ ሉዓላዊነትንና የመሬት ድርሻን ከብሔረሰብነት ጋር ያያዘ ብሔረተኛ ፖለቲካ አዕምሮ ላይ ያሳደረው ተፅዕኖ ነው፡፡ በንዑስ አንቀጹ የአማርኛና የእንግሊዝኛ ቅጂ ውስጥ የታየው የአገላለጽ ልዩነትም ሉዓላዊነትን የየብሔረሰብ ከማድረግ ፍላጎት ጋር በጊዜው የተደረገውን መጓተት የሚጠቁም የቃላት ጨዋታ ይመስላል፡፡ እንዲያ ቢሆን ኖሮ እያንዳንዱ ብሔር፣ ብሔረሰብ ወይም ክልል በተመድ የታወቀ ይዞታ ያለው፣ የውጭ ግንኙነቱን ራሱን ችሎ የሚመራ ቁመና በኖረው፣ ኢትዮጵያም ፌዴራል ሪፐብሊክ ከመሆን ይልቅ ኮንፌደሬሽን ወይም የአውሮፓ ኅብረት ዓይነት ማኅበረሰብ በሆነች ነበር፡፡

  በኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት መሠረት ክልላዊ መንግሥታት የኢትዮጵያ አካል እንጂ በየራሳቸው ሉዓላዊ አይደሉም፡፡ አገሪቱን በጥቅል የሚመለከቱ ጉዳዮች ውሳኔ የሚያገኙት ወደየክልሎች ወርደው ታይተው ሳይሆን፣ “ተጠሪነቱ ለአገሪቱ ሕዝብ በሆነው” በተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ነው (አንቀጽ ፶፡፫)፡፡

  ከታች ጀምሮ እስከ ክልል፣ ከክልል እስከ ፌዴራል ደረጃ ያሉ የሥልጣን አካላት በሕዝብ ወሳኝነት እንዲደራጁና እንዲመሩ የደነገገ፣ ክልል ገብ ጉዳዮችን ለክልሎች፣ ክልል አለፍና ከክልል አቅም በላይ የሆኑ ጉዳዮችን ለፌዴራል ለያይቶ የሰጠ ሕገ መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን አስማምቶ ለማስተዳደር በፍፁም አያንስም፣ አይጠብም፡፡ አንዳንዶች ለልብ መከፋፈል የዳረገን ባሻ ጊዜ የራስ ክልል ከመፍጠር አንስቶ ከአገሪቱ እስከ መለየት ድረስ የሰፉ መብቶችን የሰጠው ሕገ መንግሥት ነው ብለው ያስባሉ፡፡ የዚህ ዓይነቱ አስተሳሰብ እነ እከሌን ምን አካሰሳቸው ብሎ ምክንያቱን ለማወቅ ከመሞከር ፈንታ የመክሰስ መብትን ጥፋተኛ በሚያደርግ መንገድ ውስጥ የሚነጉድ ነውና ችግራችንን ወደ ማወቅ አያደርሰንም፡፡

  የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት እንከኖች እንዳሉት አይካድም፡፡ ይህን ጉዳይ በሚመለከት ረገድ እንኳ አንቀጽ ፴፱ ውስጥ አሳሳች የሆነ አገላለጽ እናገኛለን፡፡ አብሮ ለመሆን በመስማማት ላይ፣ በአብሮነት የቅንብር አማራጮች ላይ፣ ወይም አብሮነትን በመቀጠልና በማቋረጥ ላይ የፖለቲካ ውሳኔ በመስጠትና በሕዝቦች ዕጣ/ዕድል መካከል ትልቅ ልዩነት አለ፡፡ በራስ ቋንቋ መማርና መተዳደር፣ ራስን በራስ ማስተዳደር፣ የፖለቲካ ዕጣን በዴሞክራሲ መወሰንና የመሳሰሉት በተግባር እንዲሟሉ የሚፈለጉ መብቶች ናቸው፡፡ በዚሁ ረገድ “የብሔረሰቦች የራስን ዕድል በራስ መወሰን” የሚባል “መብት”ን በዛሬው የተሳሰረ ዓለም ውስጥ ለማግኘት ብንሻ መቃዠት ይሆናል፡፡

  ብሔረሰቦች ይቅሩና አገሮችም የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የሚወስኑበት ሁኔታ ዛሬ እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ የሕዝቦች የልማት፣ የግስጋሴ፣ የሰላምና የደኅንነት ዕጣ ፈንታ በራስና በሌሎች ፍላጎት (በውስጥና በውጭ ሰበዞች ተራክቦ) የሚወሰን ነው፡፡ እስከ መገንጠል በሚደርስ ደረጃ የፖለቲካ ዕጣን የመወሰን ጉዳይ ከእነ አፈጻጸም ሥርዓቱ በሕገ መንግሥት ሠፍሮ ባለበት ሁኔታ እንኳ፣ የውሳኔው ተጨባጭነት በፍላጎትና መሥፈርቱን ለማሟላት በመቻል ብቻ አይለካም፡፡ ፍላጎትን ለሰላምና ለግስጋሴ ከማበጀቱ አኳያ በቅጡ ማመዛዘንን ይጠይቃል፡፡ በስሜት ያልታወረ ትክክለኛ ግምገማ ቀደም ተይዞ የነበር ፍላጎትን ከማጥራትም አልፎ፣ በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ ሊያስቀይር ይችላል፡፡ ግልብና የተጣደፈ ግምገማም ወደ መቀመቅ መንደርደሪያ ሊሆን ይችላል፡፡ ግምገማው ከናካቴው፣ የውሳኔ መብቴንና ውሳኔዬን በተግባር የሚያከብር ማኅበራዊና መንግሥታዊ አንጀት በዕውን አለ ወይ? ከሚል ጥያቄ የማያልፍ (አስቀድሞ ዴሞክራሲያዊ ሁኔታን የማደላደል ሥራን የሚደቅን) ሊሆንም ይችላል፡፡(በገነት ዓለሙ)
  _____________________፟!
  …የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት ከሆኑት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትና በአጠቃላይ ከ600 በላይ ከሚሆኑት የሁለቱ ምክር ቤቶች አባላት፣ አብዛኞቹ የአገሪቱን ብሔራዊ መዝሙር ስንኞች አያውቋቸውም፡፡ በመሆኑም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የአገሪቱ ብሔራዊ መዝሙር ግጥም የታተሙባቸው ወረቀቶችን ለሁለቱም ምክር ቤቶች አባላት ለማደል ተገዷል፡፡ የአንድ አገር ብሔራዊ መዝሙር ዓላማ በሕዝቦች ላይ የብሔራዊነት ስሜትን መፍጠር፣ ታማኝነትን፣ አንድነትን፣ የጋራ ሰብዕናን፣ ሰላምንና በአገር መኩራትን በሕዝቦች ወስጥ ለማስረፅ ወደር የሌለው መሣሪያ እንደሆነ የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡
  የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርም የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጭማቂ ነው፡፡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፬ የተደነገገውም ይህንኑ ያመለክታል፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር የሕገ መንግሥቱን ዓላማዎችና የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዴሞክራሲ ሥርዓት አብረው ለመኖር ያላቸውን እምነት፣ እንዲሁም የወደፊት የጋራ ዕድላቸውን የሚያንፀባርቅ ሆኖ በሕግ ይወሰናል፤›› በማለት ይደነግጋል፡፡ የምክር ቤቶቹ አባላት ምንም እንኳን ከተሰጣቸው ወረቀት ላይ እያነበቡ ቢሆንም፣ አስተካክለው ስንኙን ለመጨረስ ሲታገሉ ያይቷል።(ዮሐንስ አንበርብር)
  …ወዴት እየሄደን ነው?ይልቅ ተመልሰው ተኙ መች ተነቃና?ባልህበት ሂድ!የት ድርስ አለ!

  Reply

Post Comment