ወጣቱ በዘርና በፖለቲካ ቢከፋፈልም ስራ አጥነትን ይጋራል።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168033
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/2125405B_2_dwdownload.mp3

DW : ግጭት ጠብ በቀጠለባት ኢትዮጵያ ወጣቱ በዘር እና በፖለቲካ ቢከፋፈልም አንድ ነገር ይጋራል። ስራ አጥነትን! ይህንን የወጣቱን ችግር ለመቅረፍ መንግስት ወጣቶችን እያደራጀ ብድር ቢሰጥም በርካታ ወጣቶች አሁን ድረስ የብድሩ ተጠቃሚ ሊሆኑ እና ከስራ አጥነት ሊላቀቁ አልቻሉም።


ኢትዮጵያ ውስጥ ወጣቶች በአንዳንድ ስፍራ በዘር እየተደራጁ፣ ሌላጋ ደግሞ በተናጣል ሆነዉ ዝርፍያ እና ስርቆት እያካሄዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይነገራል።እነዚሕ ወጣቶች ያሳደሩት ስጋትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ ነዉ። በዘር እና በፖለቲካ የመከፋፈል ፈተና የገጠመው ወጣት በአሁኑ ሰዓትም እኩል የሚጋራው ስራ አጥነትን ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ  ከአራት ወር በፊት ለኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባሰሙት ንግግር ኢትዮጵያ ውስጥ የስራ አጡ ቁጥር ከ 11 ሚሊዮን በላይ መድረሱን ገልጸው ነበር። ከነዚህም ስራ አጦች መካከል ሶስት ሚሊዮን ያህሉ ወጣቶች የስራ እድል እንዲያገኙ መንግስት አቅዶ ለመስራት መዘጋጀቱንም የ2012 ዓም በጀት ሲፀድቅ ይፋ ሆኗል።
ከዚህም በተጨማሪ  በርካታ ወጣቶችን  በልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች አሰልጥኖ በ 2012 በጀት አመት 50,000 ስራ ፈላጊዎችን ወደ ዱባይ ለመካል እቅድ እንዳለም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። መንግሥት ወጣቱን የስራ እድል ለማሲያዝ ከሚጠቀመው ዘዴ አንዱ ወጣቶችን በጥቃቅን እና አነስተኛ አደራጅቶ ብድር የሚሰጥበት መንገድ ነው። በዚህ ተጠቃሚ የሆኑ ወጣቶች ባይጠፉም አሰራሩ ብዙ ፈተናዎች እንደገጠሙት ነው ከዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዶቻችን የምንረዳው። ዶይቸ ቬለ DW ከወረባቦ ወረዳ ያነጋገራቸው ሁለት ወጣቶች እንደሚሉት ከሆነ ብድር ለማግኘት ከየቀበሌያቸው ተመልምለው ብድራቸውን ሲጠባበቁ 10ኛ ወራቸው ነው።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.