ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የኦሮሞ ሴቶች ማህበር አባላት ጋር ተወያዩ

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የኦሮሞ ሴቶች ማህበር አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የኦሮሞ ሴቶች ማህበር አባላት ጋር ተወያዩ።

በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ የኢሬቻ በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የእርቅና የመቻቻል ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በኮቪድ 19 ምክንያት የተወሰነ ቁጥር ባላቸው ሰዎች ብቻ እንደሚከበር የአባገዳዎች ህብረት መግለጹ ይታወሳል።

በዚህም የበዓሉ አንድ አካል የሆኑት ሴቶች የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል ህግና ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ባህላዊ እሴቱ ሳይጓደል እንዲከበር የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ተገልጿል።

በመድረኩ ላይ ሴቶች በኢሬቻ በዓል አከባበር ውስጥ ያላቸዉን ሚና የተመለከተ ታሪካዊ አድምታ የታሪክ ባለሙያ በሆኑት አቶ ስንታየሁ ቶላ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በትዝታ ደሳለኝ

The post ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የኦሮሞ ሴቶች ማህበር አባላት ጋር ተወያዩ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply