ወ/ሮ ዳግማዊት ከሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ጸሃፊ ዶ/ር ፋንግ ሊዩ ጋር ተወያዩ

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%88-%E1%88%AE-%E1%8B%B3%E1%8C%8D%E1%88%9B%E1%8B%8A%E1%89%B5-%E1%8A%A8%E1%88%B2%E1%89%AA%E1%88%8D-%E1%8A%A0%E1%89%AA%E1%8B%AC%E1%88%BD%E1%8A%95-%E1%8B%B5%E1%88%AD%E1%8C%85%E1%89%B5-%E1%8B%8B/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ከሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ዋና ጸሃፊ ዶክተር ፋንግ ሊዩ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ የመከሩ ሲሆን፥ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መስማማታቸውም ተገልጿል።

ዶ/ር ፍንግ ሊዩ በአቪዬሽን ዘርፉን እስካሁን በተሰሩ ስራዎች እና በመጡ ለውጦች ላይ ግንዛቤ ይዘው ይበልጥ ለማጠናከር እና በጋራ ለመስራት እንዲያስችላቸው በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርጉ በሚኒስትሯ ግብዣ ቀርቦላቸዋል።

ዶ/ር ፍንግ ሊዩም ከወይዘሮ ዳግማዊት የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመላክታል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.