‹‹ውህደቱን በስምምነት ማጠናቀቁ ይጠቅማል፤ ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም›› ፕ/ር መረራ ጉዲና

Source: https://mereja.com/amharic/v2/169463

የኢህአዴግ ውህደት በስምምነት ላይ መመስረቱ ለአገሪቱና ለህዝቧ ጠቃሚ መሆኑን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ተናገሩ፡፡ ምርጫውን ማራዘምም አገሪቱ ላለችበት ሁኔታ መፍትሔ እንዳልሆነና ለበለጠ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችልም ገለጹ፡፡
ፕሮፌሰር መረራ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የኢህአዴግ እህት ፓርቲዎች አንድ ውሁድ ፓርቲ የመሆን ሃሳባቸው የራሳቸው ቢሆንም እንደ ፖለቲከኛ ግን በስምምነት ቢዋሀዱ ይጠቅማቸዋል፡፡ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ሊጥላቸው ይችላል። የፓርቲዎቹ ለመዋሃድ አለመስማማት የለውጡን መንገድ እንዳያስትና እንዳያደናቅፍ፣ አገሪቷንም ወዳልተጠበቀ ቀውስ ውስጥ እንዳያስገባ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ፓርቲዎቹ ከራስ በላይ ለአገር ማሰብና ለውጡም እንዳይጨናገፍ የራሳቸውን ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አብራርተዋል፡፡

ለተጨማሪ ንባብ ሊንኩን ይጫኑ

‹‹ውህደቱን በስምምነት ማጠናቀቁ ይጠቅማል፤ ምርጫውን ማራዘም መፍትሔ አያመጣም›› ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.