ውስብስቡ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርና የቁጥጥር ድክመቶች የደቀኑት አገራዊ ፈተና

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168845

ብሩክ አብዱ Reporter Amharic 

ውስብስቡ ሕገወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርና የቁጥጥር ድክመቶች የደቀኑት አገራዊ ፈተናአፍሪካ ከምዕራብ እስከ ምሥራቅ፣ ከሰሜን እስከ ደቡብ በግጭቶች ስታናወጥ የኖረችና ያለች አኅጉር ስትሆን፣ ይኼ የተንሰራፋ ግጭትና ብጥብጥ ውስጣዊ ችግር ላላቸውም ሆነ መጠነኛ መረጋጋት ለሚታይባቸው አገሮች ዳፋው መትረፉ ደግሞ አልቀረም፡፡ በተለይ በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ ፍላጎቶች የተተበተበውና የግጭቶች መናኸሪያ በሆነው የአፍሪካ ቀንድ ችግሩ ጐልቶ የሚታይ ነው፡፡ ግጭት፣ ጦርነት፣ ብጥብጥና የመሳሰሉ ቀውሶች የቀጣናው መለያ እስከ መሆንም ደርሰዋል፡፡ ቀጣናውን ያጠኑና የግጭትና የብጥብጥ አዙሪቱ ማለቂያ አልባ ሆኖ ያገኙት ተመራማሪዎች፣ በቀልድ መልክ ቀጣናው ይኼን ያህል ብጥብጥ እያስተናገደና አዳዲስ ግጭቶችና ጦርነቶችን እየተፈለፈሉ ያለው በስሙ ሳቢያ ሊሆን ስለሚችል፣ ‹‹የአፍሪካ ቀንድ ማለቱን እንተው እንዴ?›› ሲሉም ተደምጠው ያውቃሉ፡፡
እነዚህ ደርዛቸው የሰፋ ቀውሶች መዘዛቸው የሰፋና ዘላቂ የሆነ መፍትሔ ለመስጠት አዳጋች ከመሆኑም ባለፈ፣ ወደ ሌላው አካባቢ በቀላሉ እንዲዘዋወሩና እንዲሰፉ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች አንዱ ሕገወጥ የመሣሪያ ዝውውር ነው፡፡ ‹‹የአነስተኛ የጦር መሣሪያዎች ሥርዓትና ኢተገቢ አጠቃቀም በምሥራቅ ጎጃም›› በሚል ርዕስ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደኅንነት ተቋም የማስተርስ ዲግሪ መርሐ ግብር የመመረቂያ ጥናት የሠሩት አቶ አዕምሮ ጠናው፣ ይኼንን እውነት እንደሚከተለው ያስቀምጡታል፡፡
‹‹የአነስተኛ የጦር መሣሪያዎች ሥርገት በአፍሪካ ቀንድና በታላቁ የሐይቆች ከባቢ ቀጣይና አድብን የሆኑ ጥረቶችን ሲያስከትሉ ይታያሉ፡፡ በተለይም የግጭት ቀጣና በሆኑት እንደ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ሰሜናዊ ኡጋንዳ የአነስተኛ መሣሪያዎች በአመፆች ሳቢያ የሚከሰቱ ሞቶች ምክንያት ናቸው፤›› የሚሉት አቶ አዕምሮ፣ ‹‹የአነስተኛ መሣሪያዎች (Small Arms and Light Weapons) ሕገወጥ ዝውውር ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች እጅግ የበዛ ነው፡፡

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.