ዓለም አቀፉ ኮርድ ኤድ በጎ አድራጎት ተቋም ለኢትዮጵያ 67 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮቪድ መከላከያ ግብዓት ድጋፍ አደረገ።ኮርድ ኤድ የተሰኘው አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅት ግምት ዋጋው 67 ሚሊ…

ዓለም አቀፉ ኮርድ ኤድ በጎ አድራጎት ተቋም ለኢትዮጵያ 67 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮቪድ መከላከያ ግብዓት ድጋፍ አደረገ።

ኮርድ ኤድ የተሰኘው አለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅት ግምት ዋጋው 67 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ ለጤና ሚንስቴር ድጋፍ አድርጓል።

የኮርድ ኤድ ካንትሪ ዳሬክተር አኪንዪ ዋሌንደር በድጋፍ ርክክቡ ወቅት እንደገለፁት የኔዘርላንድ መንግስት እና አውሮፓ ህብረትን ጨምሮ ለዚህ ድጋፍ የተባበሩ ተቋማትን አመስግነዋል።

ድጋፉ ከንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች በተጨማሪ በኮቪድ-19 ዙሪያ ያተኮሩ የመረጃ ግበዓቶችም ተካተዋል።

በተጨማሪም የጤና ባለሙያዎች የሚጠቀሟቸው የህክምና ግባቶችም አካታች ያደረገ ሲሆን የግብዓት ስርጭቱን ማገዝ የድጋፉ አንድ አካል መሆኑን ገልፀዋል።

በርክክብ መረሀ ግብሩ ላይ እንደተገለፀው ቁሳቁሶቹ ለአማራ ለኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች ይከፋፈላል ያሉ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግበዓቶቹን ወደ ክልሎቹ በማሰራጨት ረገድ እንደሚያግዝ ዋሌንደር ተናግረዋል።

የጤና ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በበኩላቸው ኮቪድ-19 የጤናውን ሴክቴር ብቻም ሳይሆን በኢኮኖሚው ላይም ጫና የፈጠረ ቢሆንም ኢትዮጵያ የተሻለ አፈፃፀም አሳይታለች በማለት ተናግረዋል።

ይህም የኔዘርላን ኤምባሲን ጨምሮ በርካታ ለጋሽ አካላት ለጤና ሴክተሩ ባለማቋረጥ ለሴክተሩ ድጋፍ በማድረጋቸው መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ተቋማቱ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኔዘርላንድ አምባሳደር ሄንክ ጃን ባኬር በበኩላቸው የኔዘርላንድ መንግስት በኢትዮጵያ የጤና አገልግሎቶች በተሟላ መልኩ ለዜጎች ተደረሽ እንዲሆ በቀጣይ አስፈላጊ ድጋፎችን ማድረጉን እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ ጭነት አገልግሎት ዳሬክተር አቶ ፍፁም አባዲ እንዳሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቫይረሱን ስርጭት በመከላከል እረገድ የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ በፕላኔቷ ለሚገኙ ዜጎች ተደራሽ መሆን ችሏል ብለዋል።

በመድረኩ የሶስቱም ክልል ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በንግግራቸውም ክልሎች ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ባለበት በዚህ ወቅት ይህ አይነቱ ድጋፍ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በዚህ ድጋፍ የኔዘርላንድ መንግስት 58 በመቶ ድርሻ ሲይዝ ኮርድ ኤድ ፤ ደች ሪሊፍ አልያንስ እና የአውሮፓ ህብረት ቀሪውን ሸፍነዋል ተብሏል።

በደረሰ አማረ
ጥቅምት 6 ቀን 2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply