ዓለም ዓቀፉ ፖሊስ ኢንተር ፖል የሸሹ ወንጀለኞችን በሚይዝበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር መከረ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75215

የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ዋና ጸሃፊ ጀርገን ስቶክ ጋር ወንጀለኞችን መያዝ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

ሚኒስትሯ የኢንተርፖል ደንብ በሚፈቅደው መሰረት በሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በህገወጥ የሠዎች ዝዉዉርና ሌሎች ወንጀሎች የተጠረጠሩ የትም ሀገር እንዳይደበቁ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከድርጅቱ ዋና ጸሃፊ ጋር ተወያይተዋል።
የኢንተር ፖል ዋና ፀሐፊ ጀርገን ስቶክ ዓለማቀፍ የመረጃ ልውውጥን በማዳበር ወንጀልፈፅመው ከሀገር ሀገር የሚዘዋወሩ ወንጀለኞችን እንዴት መያዝ እንደሚቻል በጋራለመስራት መምጣታቸውን ገልጸዋል፡፡
ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንጀሎችን በተለይ ከአየር መንገድ፣ ከጉምሩክና ከስደተኞችጋር ተያይዞ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በመከታተልና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለሚመለከተውየአባል ሃገራት አሳልፎ ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መክረዋል።
አንድ የመረጃ ቋት ኑሮ ሃገራት በምን አግባብ መጠቀም እንዳለባቸው ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚልና ጀርገን ተወወያይተዋል።
በተለያዩ ወንጀሎች የሚሳተፉ ሰዎችን የፊት ገፅታቸውንና የጣት አሻራቸውንበመውሰድ መረጃውን ከሀገራት ጋራ በመለዋወጥ ወንጀለኞችን ለመያዝ የኢትዮጵያመንግስት ድጋፍ እንደሚያሰፈልጋቸው ዋና ፀሐፊው ተናግረዋል፡፡
ወይዘሮ ሙፈሪሃት በሀገሪቱ መንግስት እያካሄደው ካለው ለውጥ ጋር ተያይዞከኢንተርፖል የግብአት፣ የስልጠና እና የቴክኖሎጅ እገዛ ለማድረግ በሚችልባቸውጉዳዮች ላይ ከሚስተር ጀርገን ጋር ተወያይተዋል።
በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስት ብሔራዊ መታወቂያ እያዘጋጀ እንደሚገኝና ከዚህጋር ተያይዞ የኢንተር ፖል የመረጃ ድጋፍን እንደሚፈልጉም ጠቅሰዋል።
ኢንተር ፖልም አብሮ ለመስራት መምጣቱ ትልቅ አቅም እንዳለው ነው ወይዘሮ መፈሪሃት የገለጹት ኢትዮጵያ የኢንተርፖል አባል ከሆነች 60 ዓመታትን ማስቆጠሯን የሰላም ሚኒስቴር በመረጃው ጠቅሷል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.