ዓባይ ሆይ አደራ! – አገሬ አዲስ

ነሓሴ 2 ቀን 2012 ዓም(08-08-2020) ዓባይም ሞላልን፣ ያሰብነው ሆነልን! ሲባል የነበረ በዘፈን ቀረርቶ፣ ምኞትና ሃሳብ በእውን ተተክቶ ደሃ ሃብታም ሳይል ያለውን አዋጥቶ፣ ለማዬት በቅተናል ግድቡ ተሰርቶ። ጨለማ አሶግዶ፣ድህነት አጥፍቶ፣ ብዙ የልማት ዘርፍ በሃገር ተስፋፍቶ፣ ተቋም ተዘርግቶ፣ፋብሪካ ተከፍቶ፣ ሠርቶ የመጠቀም ዕድል ተገኝቶ የተራበው በልቶ የጠማው ጠጥቶ በቂ ውሃ ቀርቦ በጉድጓድ በመስኖ፣ ጠፍና በረሃው የእርሻ ማሳ ሆኖ። እርሃብ ቸነፈር ቀሪ ታሪክ ሆኖ ጥቅም እንደሚሰጥ በስፋት ሲወራ፣ በግድቡ ውጤት ሲመካ ሲኮራ፣ በጉጉት ሲጠበቅ ብዙ ብዙ ሥራ፣ እንዳለፉት ሁሉ የውሸት ደመራ፣ አባይም በተራው ላም አለኝ በሰማይ እንዳይሆን አደራ! በቅድሚያ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለዚህ የህብረት ሥራ ውጤት  አበቃችሁ/አበቃን እላለሁ ዓባይ የሚለውን ቃል ጠበቅ ስናደርገው

Source: Link to the Post

Leave a Reply