ዘረኝነትን መግታትና ከጥፋት መዳን፣ ከባድ ስራ ሆኖ ነው? ወይስ እያከበድነው? ( ዮሃንስ ሰ )

Source: https://mereja.com/amharic/v2/78109

ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በጣም ከባዱ ስራ ምንድነው? ሰላም ማግኘት? ከድህነት መገላገል? ነፃ ምርጫ ማካሄድ?… ምኑ ተጠርቶ ምኑ ይቀራል! አብዛኛው ስራ እንደ ትልቅ ሸክም ሆኖ የሚታየንና መከራ የሚሆንብን ግን፣ በተፈጥሮው ከባድ ስራ ስለሆነ አይደለም። ስራው ከባድ ባይሆን እንኳ፣… በዚህም በዚያም ብለን፣ ከላይም ከታችም ተረባርበን፣ ከኋላም ከፊትም ተብትበን ለማወሳሰብ እንሯሯጣለን። ወይም ደግሞ፣ ሲተበትቡትና ሲያወሳስቡት፣ የመከራከርም ሆነ የመከላከል አቅም አጥሮን በተስፋ ቢስነት እንደነዝዛለን። ዘረኝነትን መከላከልና ከጥፋት መዳን ሲያቅተን እያያችሁ!
ከዘረኝነት በሽታ የሚገላግልና ከመዘዙ የሚያድን ሁነኛው መፍትሄ ምን እንደሆነ ጠፍቶን ነው? የዘረኝነት በሽታ፣ በራሱ ጊዜ የሚስፋፋ እርግማንና በራሱ ጊዜ የሚከስም የነፋስ ሽውታ ሳይሆን፣ ሳቢያና መዘዝ፣ መንስኤና መፍትሄ ያለው በሽታ መሆኑን መገንዘብ ከባድ አይደለም (እውነታውን አይቶ የመገንዘብ ፍላጎትና የመገንዘብ ጥረት ካልጎደለን ወይም ካላጎደልን በቀር ማለቴ ነው)።
“የጋርዮሽ ሕይወት” እንደሌለ፣… እያንዳንዱ ሰው፣ “የግል ሕይወት ባለቤት” እንደሆነ፣ እውነታው አልታይ ብሎን ነው? ወይስ ይሄን ዘላለማዊና ሁለንተናዊ እውነት፣ እንደተራ ነገር ቸል ስለምንለው ወይም ቸል ለማለት ስለምንፈልግ? እያንዳንዱን ሰው የእንደየግል ብቃቱ፣ ተግባሩና ባሕርይው መመዘንስ፣… ቀና የፍትሃዊነት መርህ እንደሆነ፣ ጨርሶ አልታይ ብሎን? እያንዳንዱን ሰው፣ የግል ብቃቱን ያህል ለማድነቅ የሚሻ ንፁህ ሰብዕናን መቀዳጀትስ፣ የተቀደሰ የግብረገብ ሃላፊነት እንደሆነ መገንዘብ ተስኖን ነው?
የሰው አእምሮና አካል፣ የግል አእምሮና አካል እንደሆነ፣… የሰው ሕይወትና ማንነት፣ የግል ሕይወትና ማንነት እንደሆነ፣… እውኑን ተፈጥሮ አይተን በቀላሉ ማረጋገጥና መገንዘብ የምንችለው በጣም ግልፅ እውነታ ነው።
ይሄውም ነው የዘረኝነት በሽታ ሁነኛ መፍትሄ። ግን፣ የበሽታ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.