ዛሚ ሬዲዮና ENN ቴሌቭዥን የፖሊስ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው

Source: http://wazemaradio.com/%E1%8B%9B%E1%88%9A-%E1%88%AC%E1%8B%B2%E1%8B%AE%E1%8A%93-enn-%E1%89%B4%E1%88%8C%E1%89%AD%E1%8B%A5%E1%8A%95-%E1%8B%A8%E1%8D%96%E1%88%8A%E1%88%B5-%E1%8C%A5%E1%89%A0%E1%89%83-%E1%8A%A5%E1%8B%A8%E1%89%B0/
mimi sibhatu

Mimi Sibhatu-FILE

ዋዜማ ራዲዮ-በመንግሥት የስለላ መዋቅር በሕቡዕ ይደገፋሉ የሚባሉት የዛሚ ሬዲዮና ኢኤንኤን ቴሌቭዥን ትናንት ከኦሮሚያ አመጽ ጋር በተያያዘ ያስተሏለፏቸው ስርጭቶችን ተከትሎ ከአድማጭ ተመልካች ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው ተባለ፡፡ ‹‹ከጠዋት ጀምሮ የስልክ ዛቻው ከሚገመተው በላይ ስለሆነ ከለላ እንዲሰጥ ተጠይቋል›› ትላለች አምባሳደር አካባቢ በሚገኘው ዛሚ ሬዲዮ ጣቢያ የምትሠራ ነባር ጋዜጠኛ፡፡ ‹‹ስልኩ ለደቂቃ አላረፈም፤ በጣም ብዙ ሰው ነበር እየደወለ የነበረው፤ በጣም ብዙ…›› ብላለች የጣቢያው ባልደረባ፡፡ የስልክ ጥሪዎቹ በአመዛኙ ጣቢያዉን በዘር ፍጅት ቅስቀሳ የሚወነጅሉ ናቸው፡፡
ዋዜማ አዲስ አበባ የሚገኙ የሁለቱን ጣቢያ ኃላፊዎች በስልክ ጠይቃ ስለጉዳዩ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተረድታለች፡፡ ኾኖም ከጣቢያው ሠራተኞችና ሌሎች ታማኝ ምንጮች ባገኘችው መረጃ መሠረት ዛሬ ከረፋድ ጀምሮ ከቅጥር ጊቤያቸው ዙርያ ጥበቃ የሚያደርጉ ፖሊሶች መመደባቸውን አረጋግጣለች፡፡
ትናንት ማምሻውን የዛሚ ሬዲዮ ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› በቀድሞው አጠራር ኢሊባቡር አካባቢ (ቡኖ በደሌ ዞን ዴጋ፣ መኮና ጮራ ወረዳዎች) በትግራይና አማራ ተወላጆች ዘንድ ደርሷል በተባለ ብሄርን ያማከለ ጥቃት ዙርያ ሁለቱ ጣቢያዎች የሠሯቸውን ዘገባዎች ተከትሎ የኦሮሚያ መንግሥት ቅሬታውን ማሰማቱ ይታወሳል፡፡
ወይዘሮ ሚሚ ስብሐቱ ከአቶ ፍጹም ብርሃኔ ጋር ባደረጉት የትናንቱ ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› ውይይት የሥራ መልቀቂያ ያስገቡትን አቶ አባዱላ ገመዳን ባልተለመደ ሁኔታ ለግጭቶች መባባስ አንድ ምክንያት ናቸው ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረውባቸዋል፡፡
‹‹የአቶ አባዱላ ንግግር ለአመጽና ሁከት ግብአት ነው፣ …አመጽና ሁከት ለማስቀጠል ለሚፈልጉ ወገኖች መልዕክት የማስተላለፍ ያህል ነው፡፡ …ሕዝብን ክብሬ ተነካ ማለት ተነስ ማለት ነው…ሌላ ምንም ማለት አይደለም፡፡››ሲሉ አፈጉባኤውን የተቹት ወይዘሮ ሚሚ ስብሐቱ ምናልባት በአቶ አባዱላ ላይ በዚህ ደረጃ የሰላ ትችት መሰንዘራቸው ሰውየው ላይ በቀጣይ የሚወሰዱ ፖለቲካዊ እርምጃዎች ይኖሩ ይሆን የሚሉ መላምቶች እንዲፈጠሩ ምክንያት ሆነዋል፡፡
ወይዘሮ ሚሚ አክለው በአቶ አባዱላ ላይ በሰነዘሩት አስተያየት ‹‹…26 አመት ውስጥ በዚህ ድርጅት የኖሩ ናቸው፤ በተለይም ኦፒዲኦ የሚባለው ድርጅት የመሠረቱ ናቸው፡፡ ለረዥም ጊዜ ከጠባቦች ጋር የታገሉ ናቸው…፡፡››ሲሉ አፈጉባኤውን ካሞገሷቸው በኋላ ስማቸውን ከሙስና ጋር ለማስተሳሰር ሞክረዋል፡፡ ‹‹…እንደዚያ ቢሆንም ደግሞ በከፍተኛ ደረጃም ደግሞ የምናውቀው ነው፣ ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው ብዬ ነበር ባለፈው ጊዜም…በከፍተኛ ደረጃ ደግሞ ስማቸው በጥሩ የማይነሳባቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ…፡፡ ሲሉ አቶ አባዱላን በሾርኔ ለመንካት ሞክረዋል፡፡
‹‹…ይሄ ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው፡፡ የሕዝብ ክብር እንዴት ነው የተነካው? በምንድነው የተነካው? የሳቸው ክብር ነው የተነካው? ምንድነው እሳቸው ራሳቸውን እንደ ሕዝብ ነው እንዴ የሚመለከቱት?›› ሲሉም ወይዘሮዋ በአቶ አባዱላ ላይ ለማፌዝ ሲሞክሩ ነበር፣ በትናንቱ የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ ኢኤንኤን ቴሌቭዥን የኢትዮጵያ ቡናና የቅዱስ ጊዮርጊስን ጨዋታ በቀጥታ ሥርጭት አቋርጦ በሰበር ዜና ያቀረበው ዘገባ ‹‹በተዛባና ሐሰት በሆነ ሁኔታ ነው›› ሲሉ ያጣጣሉት የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በተመሳሳይ የዛሚ ጣቢያንም ወቅሰዋል፡፡ ጣቢያዎቹ ‹‹ግጭቱን ሊያባብሱ የሚችሉ ዘገባዎችን ከመስራት እንዲቆጠቡ›› ካሳሰቡ በኋላ ‹‹ካልሆነም ወደፊት በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናደርጋለን›› ሲሉ ለኢቢሲ የምሽት ዜና ክፍለ ጊዜ ተናግረዋል፡፡
በመንግሥትና ክልል የፖለቲካ መዋቅር በዚህ ደረጃ እርስበርስ መወነዳጀል የተለመደ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ የኢህአዴግ ማእከላዊ አስተዳደር እየላላ ስለመሆኑ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡
በቡኖ በደሌ ዞን ዴጋ፣ መኮና ጮራ ወረዳዎች በተፈጠረው ግጭት ከፍተኛ ውድመት ከደረሰ በኋላ ማምሻውን ከአካባቢው ሽማግሌዎች ጋር በተደረገ ጥረት መርገቡ እየተነገረ ነው፡፡

Share this post

One thought on “ዛሚ ሬዲዮና ENN ቴሌቭዥን የፖሊስ ጥበቃ እየተደረገላቸው ነው

 1. ” በኢሉ አባ ቦራ..ቡኖ በደሌ ፰ ኦሮሞዎችና ፫ አማራዎች ሞቱ…በሰፊ ደጎቻ ቀበሌ የ፭ ዐማሮች ቤት ተቃጥሎ አድሯል።ፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሠራዊት ወደ ጮራ የገጠር አካባቢዎች ቢሔድም የወረዳው አስተዳዳሪ ገጠር ችግር የለም፤ በከተማው አካባቢ የተወሰነ ግርግር ነበር አሁን ተረጋግቷል በሚል መልሷቸዋል፡፡በአንዳንድ አካባቢዎች ችግር ሊከሰት ይችላል በሚል የቀበሌ አስተዳዳሪዎች የዐማራ ተወላጆችን ከቤታቸው ወጥተው በቀበሌ ጽሕ/ቤቶችና በገበሬ ማሰልጠኛ ጣቢያዎች እንዲዘጉ ተደርገዋል፡፡‹‹በቂ ገለልተኛ ጥበቃ ስለሌለ በአንድ ቦታ እንደተዘጉ በጅምላ የማለቅ እድል አላቸው›› አሳሳቢ ሥጋት አለ በማለት ዛሬም ኦክቶበር ፳፬ /፳፲፯ ዲማ ጋዮ በተባለ አካባቢ በዐማሮች ላይ የሚደርሰው ጥቃት በርትቶ መዋሉን የሚገልጹት ተጎጂዎች በሁለቱም ወረዳዎች ከ፲፭ ሺህ በላይ ዐማሮች መፈናቀላቸውን የሚገልጹት ምስክሮች በምግብ እጦት የታመሙ ሕጻናት ሁሉ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡” ሙ/ተ
  ___________________!
  __ ይህ ሁሉ በኪራይ ሰብሳቢዎች የተቃጣ ነው ሲሉ አቶ አዲሱ አረጋ ያረጋጋሉ!? ማፈናቀል ወይም የሜንጫ ጭፍጨፋ የሱማሌና የኦሮሞ ባሕልና ወግ አደለም የሚሉት አቶ አዲሱ ኪራይ ሰብሳቢዎቹ የየት ሀገር ሰዎች እነደሆኑ አይጠቅሱም!? ይልቁንም በኦሮሚያ በሚባል ከልል የተገኘ ሁሉ መጤና የምኒሊክ ሰፋሪ ተብሎ ስለሚፈረጅ የከንባታ ተወላጆችን አስረው አማራን ገደሉ ብለው ለሚዲያ ማቅረብ በራሱ ሰብዓዊነት እና ሕግን የተከለ ውንጀላ አደለም!። እነኝህም ታሳሪዎች የሚሞግትላቸው ሰው የሆነ ሰው ያስፈለጋቸዋል!።

  **ኢንን ቲሌቪዥንና እና ዛሚ ራዲዮ ላይ የተነሳ የፌደራሉ የኮምኒኬሽን ሚ/ር እና የክልሉ ቃል አቀባይ ተቀናጅተው ያቀረቡት ጠንካራ ትችት/ከስ/ዛቻ/ማስፈራሪያ ምን እደሆነ አለየትም። ግን ይህ ዳውን ዳውን ወያኔ! ዴሞክራሲ! ፊሪደም! ነፃ ፕረስ ! እየተባለ ተቃዋሚ/ታቋቋሚ ተብዬዎች በተለያዩ አህጉሮች የሚጮኸው አያድርገውና ወደፊት ሥልጣን ቢኖረው ሚዲያውን ቢቆጣጠር ችግሮችን ለመደበቅ፡ ለማጥፋት፡ ለማዛባት ከሆነ ከደርግ/ኢህአዴግ ተቋዋሚው በምን ሊለይ ነው!? ማናቸውም የሕዝብ ጉዳይ በወቅቱ ጉዳዩ ለሚመለከተው ባልሥልጣን አካልና ችግሩ ለደረሰበት ወገን ማድረስ ወይም የሀገር ሠላምና የሕዝብ ደህንነት ለሚያገባው ዜጋ ነቅቶ እንዲጠብቅ በሰበር ዜና ማቅረብ ወንጀሉ የት ጋ ነው? የእንግሊዙ አርሰናል ቸልሴን አሸነፈ በሚል ሰበር ዜና ነው ወጣቱ የነፈዘው ብላችሁ ነው? ሕዝቡ የሚፈለገው የስኳርና ዘይት መጣ መብራት ይጠፋል ኢንተርኔት ይቋረጣል ሰበር ዜና ብቻ ነው ? መንግስት ይህንን ጭፍጨፋ፡ ንብረት ማወደምና ማፈናቀል ከአንድ ወር በኋላ ቢያወራው ጥሩ ነበር ? ማናቸውም ኦሮሚያ ውስጥ የሚጠፋ የሰው ሕይወት የንብረት ውድመት ሁሉ ጸጋ ሲሆን በኦሮሞ ላይ የሚደርስ ሁሉ የዘር ጥፋት የዓለም መጨረሻ እያደርጉ ማቅረብ ዙሪያውን የበቀል ሐውልት ማቆም እጅግ በጣም አሳፍሪና እርባና ቢስነት ነው።

  ** በዚህ አጋጣሚ ግለስቡ የዘር ወይም የፖለቲካ ቱማታ ውስጥ የገባሁ ስላልሆነ በሕግ አንጻር ..የሕዝብ ግንኝነት ኅላፊው አቶ ነገሪ ሊንጮ…ወይም አቶ አዲሱ እረጋሳ የፌደራላዊ ሥርዓቱ ምንነትም ሆነ፡ የሚዲያ ሕግ አጠቃቀም ሥርዓትን የሚቃረን ጉዳይ ገጥሟቸው ሳይሆን ጄነራል አባዱላ የሥራ ማቆም ምክንያት በሚዲያ የሰጡት ‘ዝግ የሆነ ዓረፈተነገር’… “ሕዝቤ ስለተጎዳ..ይህን ያህል ሥልጣን ይዤ ሕዝቤ ሲናቅ እያየሁ፡ በዚህ ባለሁበት ሁኔታ መቀጠል ስላልቻልኩ” ያሉት ግልፅ አደለም? አልተብራራም? የተባለው ዓረፍተነገር የበታችነት ስሜትን አጭሮባቸዋል።

  __ በመሠረቱ የቀደሞው አፈጉባኤ የአሁኑ የኦህዴድ ልዩ መልክተኛ ጄነራል አባዱላ ገመዳ በዛሚ ኤፍ ኤም፤ ወይም ኢ ኢን ኢን ቲቪ፤ ቀርበው መሞገት የውዴታ ግዴታቸው ነበር። ግን አሁን ጋሻ ጃግሬዎቻቸውን ጃስ ብለው ሥሜ ለምን ተጠቀሰ? ከዚህ በፊትም ስለአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የተቃወምኩት ለኦሮሞ ሕዝብና ለወከልኩት ፓርቲ ኦህዴድ ነውና ሕዝቤን አጯጩሁልኝ ካሉ መዘዝ አለው !? ዓሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል…! ለኦሮሞ ሕዝብ አሳቢ “የከተማና መሠረተ ልማት መስፋት አይከለክልም/አይቃወምም ሕዝብ አያሳምፅም፡ የሚከለክለው/ የሚያሳድመውና ንብረት የሚያጠፋው፡ ኪራይ ሰባሳቢው አካል ነው።
  *(ኪራይ ሰብሳቢ ሊኖር..የሚከራይ መሬት/ንብረት አለ፡ተጠቃሚ/ተከራይ አለ፡ደላላ/አቀባባይ/አዋዋይ/ጠባቂ አለ)፡፡

  * አባዱላ የማን ወገን ሆነው የአዲስ አበባን መስፋት ሲቃወሙ፡ አዲስ አበባን ፊንፊነ ለመቀየር…የመንገድና የሥራ ቋንቋ መለወጥን ከዲሲ/ከሜኒሶታ የሜንጫ አብዮተኞች ጋር ለምከር የነፃ አወጭ ሚዲያ ሲያቋቁሙ/ሲኳትኑ (አሸባሪ) ሳይባሉ፡ጭራሽም ከአሜሪካ አውስትራሊያ ካናዳ ‘ሬድ ኢንዲያንስ ‘አክት ቃል በቃል ነጠላ ሰረዝ ሳይቀር ኢንዲጂነስ (ሜጫና ቱለማ) አክት የፊንፊነ ሕግ አርቅቀው በግላቸው ፓርላማ ለማፀደቅ ሲሰሩ ኖሩ? በኩራትም ኦሮሞ በአሁኑ ወቅት ከውስጥም ከውጭም አንድ ነው ሲሉ ተኩራተዋል።ኦፌኮ እና መድረክም ይህንኑ ሲደነፉ ነበር ውጭ ማን አለ?
  ከህወሓት/ኢህአዴግ የኮበለሉ ሥልጣን ጥመኞች ወይስ ሀገር በመሠርሠር ህወሓት ውጭ እንዲሠረስሩ ያሰማራቸው?
  ____ስለሆነም “እርጥብ እሬሳ ደረቅ እሪሳ አስነሳ” ከመባሉ በፊት እነኝህ አዳዲስ ዶ/ር..ፕሮፍ..ኢንጂነር ወጣት መሪዎች ቤታቸውን በደንብ ቢያፀዱ የተሻለ ነው። ይህ ቱሪናፋ/ቱማታ ያዋርዳል፡ በሕግ አንጻር ይሸነፋሉ?ይሾፍባቸዋልም…ቢቻል በፍቅር ቢተላለፉ ይበጃል። በፖለቲካውም ቢሆን አማራና ኦሮሞን ነገድን ማቀራረቡን አላወቁበትም። ወጣቱ ደምህ ደሜ ነው! ጣና ኢትዮጵያ ኬኛ! ሲል በልጧቸዋል… ኦሮሞ በተንኮል ተከልሎ በራሱ ወገን የዜሮ ድምር የ፵፮ ዓመት ልፊያ ያለቀው አልቆ የቆመው እየተራበ የበይ ተመለካች ሆኗል!! ዛሬም ምንይልክ!?

  **አማራ ብዙ ቦታ በገሃድ በአዋጅ ተጠቅቷል…ለደቡብም ክልልም ቢሆን ህወሓት/ትግሬ ፀብ ቀስቃሽም፡ አባባሽም ቢሆን ተጠያቂው የክልሉ አስተዳዳሪ ኦህዴድ ብቻ ነው። ባለፉት ፳፯ ዓመት ጉዞ በአብዛኛው ሁከት፡ ሰውና ንብረት ሠላም የጠፋው፡ ኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር ውስጥ ነው፡ ያ..ማለት ክልሉ ለማስተዳደር የተሰጠውን ሕዝብና ክልላዊ ግዛት(መሬት) በሠላምና በዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ሕሳቤ መምራት ባለመቻሉ ካርታው ተቀንሶ፡ የሞግዚት አስተዳደር ይሾማል፡ ወይንም አካባቢው ለአስተዳደር አመቺና ለሕዝቦች አብሮ መኖር ዋስትና የሌለው፡ ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና፡ ድህነትን ለመዋጋት አስጊና አደገኛ በመሆኑ ይህንን የጫካ ልዩ ጥቅማጥቅም ውድቅ ያደረገ ኦሮሚያ ሰፈርን ልክ እንደጋራ ጠላታቸው ሻቢያ/ህወሓት/ኦነግ/ኦብነግ በኅብረት/ተፈቃቅረው/ተፈቃቅደው የሸዋ ጠቅላይ ግዛትን አራት ቦታ እንደቆረሱና እንደበሉት ሁሉ፡ ኦሮሞሙያን አራት ቦታ ቆርጦ ከመቀነስ ሌላ አማራጭ የለም። ማናቸውም ዜጋ በኢትዮጵያ ተዘዋወሮ መኖር ወይንም ቋሚ ንብረት መሥርቶ ወልዶ ከብሮ የማይኖር ከሆነ ገዜው ባርነትና አፓርታይድን አይፈቀድም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መቀጠል የለባትም! ከቀድሞው (አኅዳዊ) ሥርዓት የተሻለ ፌደራላዊ ሥርዓት ማለት ሀገራዊ እሴትና ሉዓላዊነትን በጎጥ፡ በቋንቋ፡ እየጠበቡ አደለም፡ አስተዋይና በጋራ ሠርቶ፡ በጋራ ለማደግ ፍትሃዊ የሀብት ተጠቃሚ ለመሆን ማረጋገጫ፡ ሲባል ብቻ በቀዬው ተወላጆች ይተዳደሩና ሁሉም የዕድገት ተፎካካሪ ይሁን ማለት ነበር። አሁን ግን አዝማሚያው ክልሌ፡ ሕዝቤ፡ መሬቴ፡ባሕሌ፡ ቋንቋዬ አትድረሱብኝ፡ አትበክሉኝ…ራስ ገዝ ነን፡ በፌደራል መንግስት አንመራም! ፅንፎችም ጎልተው ወጥተዋል ይህ ‘ ከዕውቀት ሳይሆን ከዕብደት’ ነው!።አራት ነጥብ።
  እየተስተዋለ መጪው ቀን ይበለጣል ለሁሉም ሠላም!

  Reply

Post Comment