ዛሬ በተጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ኤሌክትሪክና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀናቸው

Source: https://fanabc.com/2018/10/%E1%8B%9B%E1%88%AC-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8C%80%E1%88%98%E1%88%A8%E1%8B%8D-%E1%8B%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3-%E1%8A%A8%E1%89%B0%E1%88%9B-%E1%8B%8B%E1%8A%95%E1%8C%AB/

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 13ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር ዛሬ የተጀመረ ሲሆን፥ ኤሌክትሪክና ኢትዮጵያ ቡና ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ስታዲየም 8፡00 ሰዓት ላይ የተገናኙት መከላከያና ኤሌክትሪክ ሲሆኑ ሃብታሙ መንገሻ በመጀመሪያው አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ኤሌክትሪክ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ሁለተኛው ጨዋታ ደግሞ 10፡00 ሰዓት ላይ የተከናወነ ሲሆን፥ ኢትዮጵያ ቡና አዳማ ከተማን 3 ለ 2 አሸንፏል

ለኢትዮጵያ ቡና ግቦቹን ሱሌይማን ሎክዋ እና ቃልኪዳን ዘላለም በመጀመሪያው አጋማሽ ሲያስቆጥሩ  ክሪዚስቶም ንታምቢ ደግሞ በሁለተኛ አጋማሽ ላይ ቡድኑን አሸናፊ ያደረገችውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

ለአዳማ ከተማ ደግሞ ሁለቱንም ግቦች በረከት ደስታ በመጀመሪያው አጋማሽ ላይ አስቆጥሯል፡፡

ጨዋታው በምድብ ሁለት ነገም የሚቀጥል ሲሆን፥ 8፡00 ሰዓት ላይ ኩዋራ ዩናይትድ ከወላይታ ዲቻ፤ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ፋሲል ከነማ ከጅማ አባ ጅፋር ይጫወታሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ውድድር መርሃ ግብር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጥቅምት 11 ድረስ ይቀጥላል፡፡

 

 

በአብርሃም ፈቀደ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.