የህብር ፓርቲ ምስረታ ጉባኤ ተካሄደ ።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/117282

የአምስት ፓርቲዎች ውህድ የሆነው የህብር ፓርቲ ምስረታ ተካሄደ ።
በአገር ውስጥና በውጭ አገር ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ አምስት ፓርቲዎች አገራዊ ፓርቲ ሆነው ውህደት ፈጽመዋል፡፡
ህብር ፓርቲ በዛሬው ዕለት የምስረታ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡

በዛሬው ዕለት ውህደት የፈጸሙ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ንቅናቄ፣ ቱሳ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት፣ የኦሞ ህዝቦች ዲምክራሲያዊ ህብረት እና ደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮከቦች ቅንጅት ናቸው፡፡
ተመሳሳይ ሀሳብ የሚያራምዱ ፓርቲዎች መጣመራቸው ለአገሪቱ ፖለቲካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው እና ለህዝቡም የተሻለ አማራጭ ይዘው እንደሚቀርቡ በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ፓርቲው የመተዳደሪያ ደንብ እና የፖለቲካ ፕሮግራማቸውን ዛሬ በይፋ ለተከታዮቻቸው ያሳውቃሉ፡፡
የህብር ፓርቲ የሚከተለው ለዘብተኛ ሊብራል ርዕዮተአለም እንደሆነ አሳውቋል፡፡
( EBC )
Image may contain: 8 people, people sittingImage may contain: 10 people, people sitting

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.