“…..የህዝቡን ጥያቄ በመቀልበሳቸው በድርጅቱ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል…” – ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/127537

“…..የህዝቡን ጥያቄ በመቀልበሳቸው በድርጅቱ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል…” ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌ ለአማራ ቲቪ ስልክ ደውለው ስለ ቅዳሜው ክስተት አስተለለፉት በተባለው መልዕክት ከላይ የተጻፈውን ሲናገሩ ይደመጣሉ።

Share this post

One thought on ““…..የህዝቡን ጥያቄ በመቀልበሳቸው በድርጅቱ አመራሮች ላይ እርምጃ ተወስዷል…” – ብ/ጀነራል አሳምነው ጽጌ

 1. ሙሉ ቀን ሰጠዬ ሰጠን!!
  የንግግሩ አጀማመር እና ጋዜጠኛው የሚተውነው በፍፁም አይገናኝም። መጀመሪያ እውነት በማስታወሻ እያነበቡ አይተረክም። ደዋዩ እርምጃ ወስደናል!…ብሎ ጀምሮ ብ/ጄነራሉን ዝርዝሩን ንገረኝና ይለዋል!? ዛሬ ሞቶ የተቀበረውን ብ/ጄ አሳምነው ጽጌን ግን እሳቸው እያለ ያወራል!? ይህንን ለሱ በስልክ ከሚዘረዝርለት ግንባሩን ብሎ እራሱ በቀጥታ ስርጭት መንገር አቅቶት ነው? መንግስት የሚፈነቀለው ሚዲያ ቢሮ፡ አየር ጣቢያና መከላከያ ተቋማት ሳይከበቡ ነው? የሟች የአንባቸው መኮንን ሶስተኛ ሹፌር መኪናውን አቁመህ ከገባህ በኋላ ምን አየህ ? ቢሉት ” ኮ/ል አለበል አማረን ቁጭ ብድግ እያስደረጉት ሲገርፉት አይቻለሁ አለ። ይህ ጋዜጠኛ ከመጀመሪያ ንግግራቸው በኋላ ንጉሱ ጥላሁን ጋ ደውሎ ተናግሮ ሲደውልልህ ድምፁን ቅዳ ብሎታል(ለምን አልቀዳኽውም ሲለው ሰሞኑን ተፈላሰፈብን ለበል?!
  …ይህ ቅጂ ግን ኢንተሪቪው ላይ ፊልሙ ሲንሸራተት ተመልከቱ! ጋዜጠኛውና ብ/ጄ አሳምነው ፅጌ ቃለምልልስ ተቆርጦ የተቀጠለበት ቦታ መልሱ ከጥያቄው ቀድሟል…ኮፒ ፔስት (ቆርጦ ቀጥል) ነው።
  *********************************1:12 ሰከንድ
  [{ያ እርምጃ ወስደናል ( ) ዝርዝሩን ንገረኝና… ምን እንዲህ
  በአዴፓ አመራሮች ላይ ኦረዲ(ወዲያው)… የሕዝቡ ሰላማዊናየመኖር መብቱ ጥያቄ ውስጥ ስለገባ የሕዝብ ጥያቄ ማንሳት በመቸገራቸው፤ አትሊስት(ቢያንስ) የሕዝቡን ጥያቄ በምቀልበሳቸው በድርጅቱ አመራሮች ላይ ኦረዲ(ቀደሞ) እርምጃ ተወስዷል ያ! (አዎን!) እንዳትደነግጥ}

  እዚህ አካባቢ ሶሳይቲው (ማኅበረሰቡ) ወደቤት እንዲገባ የአካባቢው የፀጥታ ኀይልና ሚሊሻ ደሞ እራሱን እንዲቆጣጠር …( ) ትላለህ፡ ያ..(አዎ) ወደቤቱ ሁሉም ባሕርዳር በተለይ ሁሉም የሚሰጠውን መመሪያ እንዲጠብቅ ኧ
  ከፀጥታ ቢሮ በቃ። ካሜራ ወይ እንላክ ? ላክ ገስት ሐውስ( እንግዳ ማረፊያ) }]
  ************************** ስጥ እግዲክ
  አንድ አማራ ብርጋዴር ጄነራል ይህንን የተፈነቃቀለ አማርኛ አወራ? በእየስብሰባ አዳራሹ የሚያደርገውን ንግግር ያደመጠ ሰው ይፍረድ…ኢትዮጵያ በኅይለማርያም ደስለኝ ስትመራ መቆየቷ በጣም የሚገርም ነው?! ያለው ማን ነበር?
  ************************************
  ሰሞኑን ይህ ጥቁር ልብስና ጥቁር ባርኔጣ አድርገው አማራን እየመራን ነበር የሚሉ ሰዎች በእርግጥ አማራዎች ናቸውን?
  እነኝህ እውነትም ለመቶ ዓመት ጥፋታችን በደንብ ተመራርጠው የተኮለኮሉ የአንድ መንደር አጭልጎች ናቸው።
  ***********************************
  ** ሙሉቀን ሰጥዬ ሌሎች እንተርቪዎችን በደንብ ሸምድዷል፡ እስከ 11 ሰዓት ድረስ ደህና ነበር፡ በኋላ እስኪጨልም ድረስ እንጂ ሰዓቱን አያውቅም፡ንጉሱ ጥላሁን አዲስ አበባ የሰማውን ዜና እዚያወ አጠገብ ተጎልቶ ሳይሰማ ቀርቶ አርፍዶ ግን “ተኩሱ እዚህ ቢሮ ድረስ ይሰማ ነበር” ይላል።፡የሚገርመው ሜ/ጄ ” እዚህ አካባቢ ሶሳይቲው(ማኅበረሰቡ) ወደቤቱ እንዲገባ በል” አለው እንጂ “መንግስት ተፈንቅሏልና አማራ መሳዩ ብአዴን ይጠቀምበት የነበረው የመገናኛ ብዙሃን ከዛሬ ሰኔ አሥራአምስት ሃያመቶ አሥራአንድ ጀምሮ የአማራ ጭቁን ሕዝብ መጠቀሚያ ሆኗል!! አላለም በል አላለውም። ሕዝቡንም ውጣ፡ ዝረፍ፡ ግደል፡ እረብሽ ሲል አልተሰማም። ይልቁንም የፌደራሉ መንግስት በንጉሱ ጥላሁን አቀነባባሪነት ጀግና ማጥፋት ግቡ መሳካቱን ሲያወቀው ” የአማራ ክልል (መስተዳድር) መፈንቅለ ሙከራ ተካሂዶበታል ብሎ ሥራቸውን በስውር የአማራ ሚዲያ አቅረበው ወሬውን ፌደራላዊ ለማድረግ ኢቲቪ ላይ ለጥፈው ኮ/ል ዓብይ አህመድ(አብዮት) የሚሊሻ ጥብቆ ለብሶ አላዘነብን ግን እሱ አልነበርምን “በቀጥታ ጦርነት እንጀምራለን” ሲል ሕዝቡን ያደፋፈረው?! ንጉሱ ጥላሁን ጢኖ ጢኖ ኦሮሞፊያ ማወቁ የሜንጫ ድጋፍና ጥበቃ ይደረግለታል። ዶ/ር አንባቸው መኮንን የኦሮሚያን ልዩ ጥቅም ሲደገፍ፡ የትግራይና የአማራን የጋራ ጥቅም ሳይጀምር በሉት፡ የኦዴፓን የተረኝነት ልዩ ጥቅም ሰጥቶ መውሰድ የማይቀበሉና የሚገዳደሩ እንዲህ በግርግር እንደወጡ ይቀራሉ። አደለም እንዴ ዋሸሁ እንዴ? ? ?

  Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.