የህዳሴ ግድቡን በአራት ዓመታት ለማጠናቀቅ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያስፈልግ መንግሥት ይፋ አደርጋለሁ አለ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/75424

Reporter Amharic

እስካሁን ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል
በሜቴክ ተይዘው የነበሩ ሥራዎች በሙሉ ተነጥቀዋል
በ2003 ዓ.ም. በይፋ ግንባታው የተጀመረው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአምስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ የተመደበለት 80 ቢሊዮን ብር በጀት ቢሆንም፣ በተባለው ጊዜ ሳይጠናቀቅ ከመዘግየቱም በተጨማሪ ከተመደበለት በላይ ከ98 ቢሊዮን ብር በላይ መፍጀቱን መንግሥት አስታውቋል፡፡ የግደቡ ግንባታ በአራት ዓመታት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ቢገለጽም፣ ለማጠናቀቅ የሚጠይቀው ተጨማሪ ወጪ ግን ይፋ አልተደረገም፡፡
ከመነሻው 5,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ያመነጫል ተብሎ የተጀመረው የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በሒደት ወደ 6,400 ሜጋ ዋት ተሻሽሎ ግንባታው ሲካሄድ ቢቆይም፣ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) እንዲገነባ በተደረገው የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የኃይድሮሊክ ብረት መዋቅር ሥራ ከፍተኛ መጓተትና የጥራት መጓደል ሳቢያ ግንባታው መዘግየቱን መንግሥት ይፋ አድርጓል፡፡
ግድቡ የሚገኝበትን ደረጃ ለማሳወቅ ሐሙስ ታኅሳስ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. በተጠራ የውይይት መደረክ ላይ እንደተገለጸው ከሆነ፣ ሳሊኒ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ያከናወነው የሲቪል ምህንድስና ሥራው 82 በመቶ ተገባዷል፡፡ ይሁንና በሜቴክ እንዲካሄድ የተደረገው የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የብረት መዋቅር ግንባታ ሥራ ከ25 በመቶ ፈቅ አላለም፡፡ ይሁን እንጂ አጠቃላይ ግንባታ በጥቅሉ 65 በመቶ መድረሱም ተነግሯል፡፡
የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብርሃም በላይ (ዶ/ር)፣ ከህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ክፍሌ ሆሮ (ኢንጂነር) እንዲሁም ከህዳሴ ግድብ ብሔራዊ ሕዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሮማን ገብረ ሥላሴ ጋር በመሆን አወያይተዋል፡፡ የግድቡን የቴክኒካዊ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.