የህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያ ምን ያደርግላታል? – ፕሬዚዳንት ትራምፕ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/168841

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ ምን እንደሚያደርግላትና ሌላ  አማራጭ ለምን እንዳልተጠቀመች ጥያቄ አቅርበው ነበር

Reporter Amharic 

ሱዳን የህዳሴ ግድቡ የሚያስገኝላትን ጥቅም በዝርዝር በማቅረብ ከኢትዮጵያ ጎን መቆሟን ዳግም አረጋግጣለች
ግብፅ ሦስተኛ ወገን አሸማጋይ እንዲሰየም ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ ተደርጎባታል
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን አሜሪካ ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወያየችበት ወቅት፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድቡ ምን እንደሚያደርግላትና ከዓባይ ውኃ ይልቅ ሌላ የኃይል አማራጭ ለምን እንዳልተጠቀመች ጥያቄ አቅርበው እንደነበር ተገለጸ፡፡
ሦስቱ አገሮች ግድቡን በተመለከተ ያላቸውን ልዩነት በውይይት እንዲፈቱ አሜሪካ በአዘጋጀችው የውይይት መድረክ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን የውይይቱ መጠናቀቅን ተከትሎ በአሜሪካ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ፣ ዋናው ውይይት ከመጀመሩ አስቀድሞ የሦስቱ አገሮች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋር ተገናኝተው እንደነበር አስረድቷል፡፡
በዚህ ወቅት ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስለህዳሴ ግድቡ ግንባታ መረዳት የሚፈልጓቸውን ጥያቄዎች፣ ለየአገሮቹ ሚኒስትሮች አቅርበው እንደነበር ተገልጿል፡፡
ለኢትዮጵያ ያቀረቡዋቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ማብራሪያ የሰጡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ “ኢትዮጵያ ግድቡ ምን ያደርግላታል?” የሚል ጥያቄ ፕሬዚዳንት ትራምፕ አንስተው እንደነበር፣ ከዚህ በተጨማሪም የዓባይን ውኃ ከመጠቀም ይልቅ “አትዮጵያ ለምን ሌላ የኃይል አማራጭ አትጠቀምም?” የሚል ጥያቄም አንስተው እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ግድቡ የታችኞቹን አገሮች ማለትም ግብፅንና ሱዳንን ምን ያህል እንደሚጎዳቸው፣ እንዲሁም ምን ዓይነት ጥቅምስ ሊሰጣቸው እንደሚችል ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበር አቶ ገዱ አስረድተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ካነሷቸው

Share this post

One thought on “የህዳሴ ግድቡ ለኢትዮጵያ ምን ያደርግላታል? – ፕሬዚዳንት ትራምፕ

  1. ትራምፕ አወዛጋቢ የእርስ በእርስ ግጭት ስለሚፈልግ ነው የኢትዮጵያ ጠላት ነው እንደዚህ አይነት ጥያቄ ዛሬ ትራምፕ ይጠይቃል የአባይ ግድብ ሲጀመር የት ነበረ

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.