የህግ የበላይነትን ለማስፈን በውስጣችን ያለውን ጥላቻ በፍቅርና ይቅርታ ማጽዳት ይቅደም

Source: https://mereja.com/amharic/v2/146295

የህግ የበላይነትን ለማስፈን በውስጣችን ያለውን ጥላቻ በፍቅርና ይቅርታ ማጽዳት ይቅደም
በኢትዮጵያ የህግ የበላይነትን ለማስፈን በፍርድ ቤት ከሚሰጠው ውሳኔ በፊት በውስጣችን ያለውን ጥላቻ በፍቅርና ይቅርታ ማጽዳት መቅደም እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ጋር በነበራቸው የቅዳሜ ጨዋታ ፕሮግራም በወቅታዊና አገራዊና ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ለውጡን ተከትሎ በውጭ ይኖሩ የነበሩ የታጠቁና ያልታጠቁ ሃይሎች በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ በይቅርታ እንዲገቡ ተደርጓል።
ይሁን እንጂ አንዳንዶች ህጉን ህጋዊ በሆነ መንገድ ተርጉመው ከመጠቀም ይልቅ ህጉን ኢ-ሞራላዊ በሆነ መንገድ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል ነው ያሉት።
“ህግ በተገቢው መንገድ ሲተገበር አብሮነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ያመጣል ካልሆነ ደግሞ ስርዓት አልበኝነትን ያሰፍናል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ።
ከኢትዮጵያ በውጭ ከሚኖሩ ሃይሎች ጋር ትጻጻፋላችሁ፣ ትነጋገራላችሁ እየተባሉ እስራትና እንግልት የሚደርስባቸው ዜጎች እንደነበሩም አስታውሰዋል።
ww.ena.et/?p=60946

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.