የሆነው ሁሉ የሆነው እንደ ኢትዮጵያዊ መኖርና ማሰብ እንድናቆም በመደረጉ ነው!  – (በድሉ ዋቅጅራ)

Source: http://www.zehabesha.com/amharic/?p=86837

በደርግ ዘመን የ11ኛ ይሁን የ12ኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ (በውል አላስታውስም) የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ሲሰራ፣ በትምህርት ቤታችን አማካኝነት ፍብሪካውን መጎብኘታችን ትዝ ይለኛል፡፡ ያኔ በጦርነት የሚባክን እንጂ፣ ለፋብሪካ የሚለማ ገንዘብና ጊዜ ሀገሪቱ አልነበራትም፤ጨቋኙን ንጉስ ያስወገዱት አብዮተኞች አብታዮዊ ባለሀብት ለመሆን እድል ሳያገኙ ነው በ17 አመት የተወገዱት፡፡ እና ፋብሪካ ብርቅ ነበር፡፡ ዋናው ነጥብ ግን፣ ‹‹ኢትዮጵያ ሀገሬ አንድ ፍብሪካ አገኘች›› […]

Share this post

One thought on “የሆነው ሁሉ የሆነው እንደ ኢትዮጵያዊ መኖርና ማሰብ እንድናቆም በመደረጉ ነው!  – (በድሉ ዋቅጅራ)

 1. * በደርግ ዘመን የአሰላ ብቅል ፋብሪካ ሲሰራ፣ በትምህርት ቤታችን አማካኝነት ፍብሪካውን መጎብኘታችን ትዝ ይለኛል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ ሀገሬ አንድ ፍብሪካ አገኘች›› እንጂ፣ ኦሮምያ አንድ ፋብሪካ ተገነባላት ያለ ይቅር፣ ያሰበም አልነበረም፡፡ አማሮች፣ ትግሬዎች፣ አፋሮች፣ ሲዳማዎች… ወዘተ. ‹‹ለእኛስ!?›› ብሎ ማጉረምረም ከልቦናቸው አልነበረም – የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ፡፡
  * የኢህአዴግ መንግስት በ፳፯ ዓመት የአስተዳደር ጊዜው ኢትዮጵያን በጎሳዊ – ክልል እንደመከፋፈል ውጤታማ የሆነበትን ተግባር አላከናወነም፡፡በክልሎች መካከል እጅግ ያልተመጣጠነ ልማታዊ እድገትም የታየው በዚሁ በኢህአዴግ የአስተዳደር ዘመን ነው፡፡ አንዳንድ የሀገራችን ክፍሎች ከሀገሪቱ ውስጥ ተቆርጠው የወጡ ይመስል በወረፋ ከሚዳረሰው የኢቢሲ የልማት ዘገባ እንኳን ሲጠፉ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ እንደ ልማታዊ ባለሀብት ሌማት በቀን ሶስት ጊዜ በየቲቪው ሲቀርቡ፣ እራሱ ኢህአዴግ በየአካባቢው እንዲዳብር ያደረገው ጎሳዊ ጡንቻ ዝም ብሎ ያየኛል ብሎ መጠበቁ የሚገርም ነው!?፡፡
  ** አሁን ኢህአዴግ ማድረግ ያለበት ‹‹የግጭቶች መንስኤ የፌደራል ስርአቱ እንዳልሆነ ምሁራን ገለጹ›› የሚል ፕሮፖጋንዳ መስራት ሳይሆን፣ የፌደራሊም ስርዓቱን ማሻሻል ወይም ሙሉ በሙሉ መቀየር ነው፡፡አራት ነጥብ።ይህ እንኳን አብሮ ሊያኖር፡ አብሮ ኳስ የማያጫውት፡አብዮታዊ ዲሞክራሲ..ዲሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት..ልማታዊ መንግስት…ከሚሉ ቱማታ ታቅቦ!
  (ህወሓት/ኢህአዴግ ብልጥ ቢሆን እያጨበጨቡ ካደነቆሩት ካድሬዎች ይልቅ እየተቆጩ/ኮርኩረው የመከሩትን ሰምቶ ቢሆን)
  በድሉ ዋቅጅራ….!

  Reply

Post Comment