የለማ-ዐብይ አንድነትም ሆነ ሁለትነት የኢትዮጵያዉያንን አጣዳፊ ሥጋት ለማቃለል አለመፈየዱ በርግጥ ያሳዝናል።

Source: https://mereja.com/amharic/v2/178381

ዐብይ «ሲነግስ» ለማ ሲወቅስ
DW : በተለይ አቶ ለማ ከኦሮሚያ ርዕሠ-መስተዳድርነት ወደ መከላከያ ሚንስትርነት ከተቀየሩ ጊዜ ጀምሮ ሁለቱ ፖለቲከኞች መቃቃራቸዉ በሰፊዉ ሲነገር ነበር።ሁለቱ ፖለቲከኞችም ሆኑ ደጋፊዎቻቸዉ ግን ልዩነት መኖሩን እስካለፈዉ ሳምንት ማብቂያ ድረስ በይፋ አልተናገሩም
መጋቢት 2010።አዲስ አበባ።
ኃምሌ 2010።ዋሽግተን።
አብዛኛዉ ኢትዮጵያዊ አንድም ሁለትም ናቸዉ አለ።ዛሬስ? ያፍታ ዝግጅታችን ጥያቄ ነዉ።አብራችሁን ቆዩ።
Lema Megerssa (DW/S. Teshome )የሩሲያን ዛራዊ ፈላጭ-ቆራጭ አገዛዝ በመቃወማቸዉ በየፊናቸዉ ከሐገራቸዉ የተሰደዱት ሁለቱ በሳል፣ ጠንካራ፣ ፅኑዕ፣ አርቆ አሳቢ ሩሲያዉያን ለንደን ብሪታንያ ላይ ፊት ለፊት ተገናኙ።1900።
«ከዚያ ወደ ለንደን ሔደ።እዚያ በሚኖርበት ባንዱ ቀን ትሮትስኪ በሩን አንኳኳ።ሌኒን በትሮስትስኪ የአቀራራብ ለዛ፣ በፖለቲካ ብስለትና እዉቀቱ ተማረከ።ወዲያዉም ቶሮትስኪን የነፀብራቅ (ኢስክራ) ጋዜጣ የአርታኤ ቡድን አባል አደረገዉ።ርዕሠ-አንቀፅ እና የፖለቲካ መጣጥፍ ፀሐፊ ሆነ።
ቭላድሚር ኢሊየች ኡሉያኖቭ (ሌኒን) እና ሊዮ ዳቪዶቪች ብሮኒስቲን (ትሮትስኪ)በክፍለ ዘመኑ መጀመሪያ ላይ የመሰረቱትን  ወዳጅነት አፅንተዉ፣ ከሞስኮ እስከ ሐቫና፣ ከቤጂንግ እስከ አዲስ አበባ ዓለምን ያጥለቀለቀዉን ርዕዮተ ዓለምን ሞስኮ ላይ ገቢር አደረጉ።
ዓለምን ለበጎ ይሁን ለመጥፎ የለወጡት ኃይለኞች ጥብቅ ወዳጅነት ግን አልቀጠለም።እንዲያዉም ጠቡ ንሩ የሌኒን ተካዮች ትሮትስኪን እስከማጥፋት በደረሰ ክፋት አሳርጓል።
አዲስ አበባ ላይ «ለትሮትስካዮቶች ዉርዉር የስታሊን በትር» እየተባለ ከመዛት መፎከሩ በፊት የማኦ ዜ ዱንግ እና የዴንግ ሺዮፒንግን፣ የፊደል ካስትሮና የቼ ጉቬራን ጥብቅ ወዳጅነትና ልዩነት የሚጥቀሱ አሉ።የኮሎኔል መንግስቱ ኃይለ ማርያምና የኮሎኔል አጥፋ አባተ፣ የመለስ ዜናዊና የነተወልደ ወልደማርያም ጓዳዊ ፍቅርን እና ጠላትነትንስ ያጤና እና ያጠናዉ አለ ይሆን?
የሌኒንና የትሮትስኪ ወዳጅነት በተመሰረተ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.