የለንደን ማራቶን በቀነኒሳ እና በኪፕቾጌ መካከል ሊካሄድ ነው

ዓለም በጉጉት የሚጠብቀው የለንደን ማራቶን በቀነኒሳ በቀለ እና በኬኒያዊው ኤሊውድ ኪፕቾጌ መካከል ጥቅምት 4 (እ.አ.አ) ይደረጋል። በዚህም ሁለቱ አትሌቶች የዓለም የማራቶን ክብረወሰንን ለማሻሻል የሚያደርጉት አልህ አስጨራሽ ፉክክር ተጠባቂ ነው፡፡ ኬንያዊው ኤሉድ ኪፕቾጌ እኤአ 2018 በርሊን ላይ (2:01:39 )በማስመዝገብ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን አስምግቦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ቀነኒሳ በቀለ ደግሞ በርሊን ማራቶን ላይ ( 2:01:41) በመግባት የኪፕቾጌን ክብረወሰን ለሁለት ሰከንድ ሳያሻሽል በመቅረቱ ሁለትኛው ፈጣኑ የማራቶን ሰዓት ባለቤት ነው፡፡ የሦስት ጊዜ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ግማሽ ማራቶን 1፡00፡22 በማጠናቀቅ ቀደም ብሎ በሞ ፋራህ ተይዞ የነበረውን የቦታውን ክብረ ወሰን ማሻሻሉ ይታወሳል። በውድድሩ አሸናፊ ለሚሆነው 313 ሺህ ዶላር ለሽልማት መዘጋጀቱ መነገሩን ኢዜአ ዘግቧል። የለንደን

Source: Link to the Post

Leave a Reply