የለውጥ ሀይሉ ተቀናቃኝ ለሁለተኛ ግዜ ሶማሊያን ለማስገንጠል ከአንዳንድ የክልሉ ሀላፊወች ጋር እየሰሩ መሆኑ ታውቀ!!!

Source: http://amharic.abbaymedia.info/archives/45441

አባይ ሚዲያ ዜና
ሱራፌል አስራት

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ የለውጥ ሀይሉ ተቀናቃኝ የሆኑት ሀይሎች በቅርቡ ከስልጣን ከለቀቁት የሱማሌ ክልል ፕሬዜዳንት ከነበሩት አብዲ ኤል ጋር በመቀናጀት የሀገሪቱን ህልውና ለመናድ ምክርቤቱ እንዲሰበሰብና አንቀፅ 39ን በመጥቀስ ከእናት ሀገሩ ኢትዮጵያ የመገንጠል ጥያቄ ለማንሳት በምክር ቤት ስብሰባ መቀመጣቸውና በለውጥ አቀንቃኙና በጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር መክቸፉ ይታወቃል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ለመንግስት ቅርብ ከሆኑ አካላት በተላከልን መረጃ መሰረት አሁንም ይህ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ የሚጥረው የለውጥ ተቀናቃኝ አድማሱን በማስፋት በሀገሪቱ ላይ ሁከትንና አለመረጋጋትን ለመፍጠር ሰፋ ያለ እቅድ ይዞ እንቅስቃሴ ለመጀመር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ከመንግስት ውስጥ አዋቂወች የደረሰን ማስረጃዋች ያሳያል።

መረጃው እንደሚጠቁመው ይህ የለውጥ ተቀናቃኝ ሀይል በባለፈው ሳይሳካ የቀረውን የሶማሌያ ክልል የመገንጠል ሙከራ አሁን በሹመት ላይ ያሉትን የሶማሊያ ባለስልጣናት በማቀናጀት እንደገና የመገንጠል ጥያቄውን ወደምክርቤቱ በማምጣት ማስፈፀም ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በአማራና በኦሮሞ ህዝቦች መካከል የተለያዩ ውጅንብሮችን በመፍጠር አለመተማመንን ለመፍጠር መሞከር መሆኑ ታውቋል።

እነዚሁ የመንግስት የውስጥ አዋቂወች እንደገለፁልን ከሆነ የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር የሚሸረበውን የጥፋት ተንኮል ለማክቸፍ በንቁ እየሰራ መሆኑን ገልፀውልናል። አክለውም ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የለውጥ ተቀናቃኞች ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጎን በመቆም ሊታገላቸው ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.