የሊቅ ዐቢይ የሰላም ኖቤል ሽልማቱ ሲፈተሽ። (ከኀይሌ ላሬቦ)

Source: https://mereja.com/amharic/v2/186422

ሊቅ ዐቢይ የሰላም ኖቤል ሽልማት በመቀበሉ የብዙዎቻችን ደስታ የሰማይ ጣራ እስከመንካት ደርሷል። አገሪቷ ያሳለፈችውንና እየተፋጠጠች ያለውን ስፍር ቊጥር የሌለውን ለሚሰማ ሁሉ ዘግናኝና አሰቃቂ ግፍና ሥቃይ ወደመርሳት ያለች ይመስላል። ሆሆታውንና እልልታውን እንደከንቱ ውዳሴ የሚያዩትም አልጠፉም። እንደነዚህ ዐይነቶቹ ሀገራዊ ክብርና ኩራት፣የሌላቸው ተብለው እየተወቀሱ ናቸው። የተሸለመችው፣ኢትዮጵያ፣ነች። ይኸንን የማይረዳ ጤንነቱ መመርመር አለበት እስከማለትም ተደርሷል።
ይቅርታ ይደረግልኝና ስለዚህ ዐጠር ባለ መልክ ጥቂት እርማትም ውዳሴም ላክልበት። በምንም መልኩ ካለመሸለም መሸለም እጅግ ደስ ይላል። እውድድር የገባ ካሸነፈ፣ ሁሌም ይደነቃል። ሊቅ ዐቢይም ተወዳድሮ አሸንፏል። ስለዚህ ቢወደስና ቢደነቅ የሚጠበቅ ነው። ከንጉሣዊ አገዛዝ መጨረሻ በኋላ፣ ኢትዮጵያን ዓለም ያወቃት በድሮ ግርማዋና ክብሯ ሳይሆን በዘቀጠ ሰብእናዋ ነው። ድርቅ፣ ራብ ሲባል እንደምሳሌ የምትጠራ ኢትዮጵያ ናት። ከዚያ ባሻገር፣ በግራ ፖለቲካ፣ ጦርነት፣ የርስበርስ ዕልቂትና ወደኋላ ቀርነትም አንደኛው እሷ ናት ቢባል ከእውነት የራቀ አይደለም። የዐቢይ ሽልማት የኢትዮጵያ ስም ከተለመደው ከሩጫ ጐን በሰላም ወዳድነትም በዓለም መድረክ እንዲነሣ አድርጓል። ከቀረው አብዛኛው የዓለም ክፍል በተለይም አፍሪቃ፣ የራሷም ብሔራዊ ቋንቋና የባህል ልብስ, እንዲሁም ጥንታዊ ጥንታዊ ሥልጣኔ እንዳላት ለማስታወቅ ከፍተኛ ዕድል ነበረው። ግን በሚያሳዝን ሁናቴ ሊቅ ዐቢይ ዕድሉን አልተጠቀመውም። በአማርኛ ፈንታ የተጠቀመው ባዕድና ቄሣራዊ ቋንቋ ነው። እንደህንዱ ታላቁ መሪ ማኅተማ ጋንዲ በብሔራዊ ልብሱ በዓለም ፊት ከማብረቅረቅ ይልቅ ካባሕርማዶ የተዋሰውን ለመልበስ መረጠ። እንደኔ ከሆነ፣ ይኸ ትልቅ ስሕተት ነው። ይኸንን ግድፈት ወደጐን እንበለውና፣ ሽልማቱ በጥሩ እንጂ በመጥፎ መታየት ያለበት አይመስለኝም።
ጥያቄ የሚነሣው የተሸለመበት

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.