የሕወሓት የደህንነት ቢሮ ሰርጎ ገብ አክቲቭስቶችን እያሰለጠነ ነው።

Source: http://www.mereja.com/amharic/562821

የሕወሓት የደህንነት ቢሮ ሰርጎ ገብ አክቲቭስቶችን እያሰለጠነ ነው። በማሕበራዊ ድረገጽ ላይ የሚንቀሳቀሱና በተለይ በሐገር ቤት የሚኖሩ ወጣቶችን በመሰብሰብ ዳጎስ ያለ ክፍያ በመክፈል በለውጥ ሃይሉ አክቲቭስቶች ላይ የስድብና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲያካሂዱ በማስተባበር እንዲሰሩ አያሰለጠነ መሆኑ ታውቋል።

ሰሞኑን እንደ ዳንኤል ብርሃኔ ያሉ የሕወሃት አክቲቭስቶች የሚከፈላቸው ገንዘብ በይፋ ከተጋለጠ በኋላ በክፍያው የጓጉና የገንዘቡ ብዛት የማረካቸው በነዳንኤል ብርሃኔ ስራ ላይ ለመሰማራት እና የለውጥ ሃይሉን አክቲቭስቶች ለመፈረጅ ለመሳደብ ስም ለማጥፋት የተመለመሉ ሰልጣኞች በኣጭር ጊዜ ስራ ይጀምራሉ ተብሏል። እነዚህ ሰልጣነው ወደ ስራ የሚሰማሩት የማህበራዊ ድረ ገጽ አክቲቭ የሆኑ ግለሰቦች እንደ አየሩ አቅጣቻ በመቀያየር የተንኮል ንፋስ የሚያነፍሱ ናቸው። የተቃዋሚ ድርጅቶች አባላት የሕዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል ይሰራሉ። እርስ በርሳቸው ይወነጃጀላሉ። ሰርገው ተመሳስለው በመግባት አዛኝ መስለው ተቆርቋሪ መስለው የጥላቻና የመለያየት ፕሮፓጋንዳ ይሰራሉ።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.