የመንግስት የልማት ስራዎችን በብቃት በማስፈፀም የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል ይገባል- አቶ ርስቱ ይርዳው

Source: https://fanabc.com/2019/10/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%95%E1%8C%8D%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8B%A8%E1%88%8D%E1%88%9B%E1%89%B5-%E1%88%B5%E1%88%AB%E1%8B%8E%E1%89%BD%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%89%A5%E1%89%83%E1%89%B5-%E1%89%A0%E1%88%9B/

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው የመንግስት የልማት ስራዎችን በብቃት በማስፈፀም የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል እንደሚገባ ተናገሩ፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ይህን ያሉት የክልሉ ገቢዎች ባለስልጣን፣ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ እና የፌዴራል ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የህግ ወጥ ንግድ እና የታክስ ህግ ተገዥነት ዙሪያ በዛጋጁት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ላይ ነው።

የስራ እድል ማስፋት፣ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እና የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ማረጋገጥ የመግንስት ትልቁ ሀላፊነት ነው ብለዋል።

የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ አጠናከሮ ለማስቀጠል የዜጎች ተሳትፎ ማጎልበት፣ የመንግስት እና የግሉ ሴክተርን ማጠናከር፣ አስተማማኝ ሰላም ማረጋገጥ እና ልማትን ማፋጠን ወሳኝ መሆኑንም ነው የተናገሩት።

ለዚህም መንግስት አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ ሊኖረው ያስፈልጋል ያሉት ምክትል ርእሰ መስተዳደሩ የመንግስት የፋይናነስ ምንጭ እንዲያድግ የተረጋጋ የኢኮኖሚ ስርዓት መፍጠር፣ ጠንካራ የታክስ አስተዳደርና ዘመናዊ እና ህጋዊ የንግድ ስርዓት መገንባት አስፈለጊ መሆኑን አብራርተዋል።

ፍትሀዊ የንግድ ስርዓት ለማስፈን የታክስ ገቢን በብቃት ለመሰብሰብ እና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴን መግታት ትኩረት የሚሹ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በታምራት ቢሻው

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.