የመከላከያ ሠራዊት አዲስ የደንብ ልብስ ወደ አገር ውስጥ ከቻይና መግባት ሊጀምር ነው

Source: https://mereja.com/amharic/v2/187889

ጨረታው አምስት ወራት ፈጅቷል፤ ከ15 የማያንሱ ድርጅቶችም እንዲወዳደሩ ተደርጓል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አዲስ የደንብ ልብስ በአንድ ወር ውስጥ የመጀመሪያው ጭነት ወደ አገር ውስጥ እንደሚገባና ከሦስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥም ሙሉ ለሙሉ ርክክቡ እንደሚፈፀም ታወቀ።

ሜጄር ጄኔራል መሐመድ ተሰማሜጄር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ
የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጄር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ እንዳስታወቁት፤ ጨረታውን ያሸነፈው የቻይና ድርጅት ከመከላከያ ጋር ውል በማሰር ልብሶቹን ማዘጋጀት ጀምሯል። የመከላከያ ሚኒስቴርም የምርት ሒደቱን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑንና የደንብ ልብሶቹን ለማዘጋጀት ጥቅም ላይ የዋለው ጨርቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው ጥራት ከፍ ያለ እንደሆነም ተናግረዋል። ልብሶቹ ተሠርተው ሲጠናቀቁ ወደ አገር ውስጥ ከሚገቡ ምርቶች ላይ ናሙና በመውሰድ የጥራት ፍተሻ እንደሚደረግባቸው አስረድተዋል።
ጄኔራል መኮንኑ ጨምረው እንደገለፁት፤ ኤታማዦር ሹሙ እና ምክትል ኤታማዦር ሹሙ በተደጋጋሚ ለብሰውት የሚታዩት የውጊያ ልብስ አዲሱ ዲዛይን መሆኑን አረጋግጠዋል።
እንደ ሜ/ጄኔራል መሐመድ ገለጻ፤ ልብሱ በተደጋጋሚ ተለብሶ እና ተሞክሮ ጥራቱ ሊረጋገጥ ከመቻሉ ባሻገር፤ በምርት ሒደቱ ከሁለት ጊዜ በላይ ባለሙያዎች እየተላኩ ናሙና በመውሰድ እና በዓለም አቀፍ ላቦራቶሪ በማስገምገም ጥራቱን መከታተላቸውንም አብራርተዋል፡፡
የሠራዊቱ የደንብ ልብስ ከሚቀየርባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ጉዳይ፤ ከዚህ በፊት የነበረው ልብስ ለሕገ ወጥ ተግባር ሲባል በተለያዩ ሰዎች እጅ በመግባቱ መሆኑን የተናገሩት ሜ/ጄኔራል መሐመድ፤ የደንብ ልብሱ የሚቀየርበት መመሪያ እንደሚዘጋጅና አወጋገዱም ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ እንደሚከናወን ተናግረዋል።
የደንብ ልብሱ አምስት ወራት በፈጀ ሒደት ዓለም አቀፍ ጨረታ በማውጣት እና ከ15 የማያንሱ ድርጅቶችን በማወዳደር የተዘጋጀ ሲሆን፤ የምድር እና የአየር ኃይልን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.