የመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎችን ጎበኙ

Source: https://fanabc.com/2019/05/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8A%A8%E1%8B%AB-%E1%8A%A8%E1%8D%8D%E1%89%B0%E1%8A%9B-%E1%8A%A0%E1%88%98%E1%88%AB%E1%88%AE%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%8C%A0%E1%89%85%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%88%9A/

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ግንባታዎችን በዛሬው ዕለት ጎበኙ።

ከጉብኝቱ በኋላም አመራሮቹ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጋር ቆይታ አደርገዋል።

በዚህም ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ በከተማዋ የሚደረጉትን “የሸገርን የማስዋብ” ፕሮጀክቶችና ለዜጎች የሚኖራቸውን ሁለንተናዊ ፋይዳ ለአመራሮቹ ማብራራታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሀሳብ አመንጪነት የአዲስ አበባን ወንዞች ዳርቻዎችን እና ሌሎች ተያያዥ መናፈሻዎችን ለማልማት ይፋ የተደረገውን ፕሮጀክት ለመደገፍ ገንዘብ ለማሳሰብ ባለፈው እሁድ “ገበታ ለሸገር” መዘጋጀቱ ይታወሳል።

ሸገርን ማስዋብ ፕሮጅክት በሚል የ29 ቢሊየን ብር ፕሮጀክት ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ከተማዋን ለሁለት ከፍለው የሚፈሱ ወንዞች ላይ ያተኮረው ፕሮጀክቱ፥ ከሰሜን አዲስ አበባ እንጦጦ ተራራ እስከ አቃቂ ወንዝ ያለውን 56 ኪሎ ሜትር እንደሚሸፍንም ታውቋል።

ፕሮጀክቱ በሶስት ዓመታት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.