የመኪና መስታወት በመስበር 600 ሺህ ብር ሰርቀው ለመሰወር የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/187879

የመኪና መስታወት በመስበር 600 ሺህ ብር ሰርቀው ለመሰወር የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ
(ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ሙዲን ከድር የተባሉ ግለሰብ በእቁብ ያጠራቀሙትን 600 ሺህ ብር የመኪና መስታወት በመስበር ሰርቀው ለመሰወር የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ዋሉ።
No photo description available.ተጠርጣሪዎች ድርጊቱን ሲፈፅሙ ባያቸው የሞተር ሳይክል አሽከርከሪ ትብብር እና በፖሊስ አባላት ክትትል ወዲያውኑ መያዛቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ጉዳዩን የሚከታተሉት ዋና ሳጅን ደነቀው አየነው በተያዙት 3 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ለህብረተሰቡ ባስተላለፉት መልዕክት ግለሰቦች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ገንዘብ ይዞ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በባንክ አገልግሎቶች መጠቀምን እንደባህል መልመድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ህብረተሰቡና ፖሊስ በተጠናከረ ትስስር ከሠሩ ወንጀልን ፈፅሞ ከህግ እንደማያመልጥ ያስመሠከረ ስራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹን እስከ መጨረሻ ተከታትለው በቁጥጥር ሥር ያዋሉትን የሞተር ሣይክል አሽከርካሪና የፖሊስ አባላትን ዋና ሳጅኑ አመስግነዋል።
Image may contain: car and outdoor

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.