የመጀመሪያው የምርጫ ክርክር ኦሃዮ በምትገኘው ክሊቭላንድ ከተማ ይካሄዳል

https://gdb.voanews.com/8A3C7D45-100B-488A-BA19-0D23FA5A3634_cx5_cy0_cw92_w800_h450.jpg

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕንና ዲሞክራቱን የቀድሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ፊት ለፊት የሚያጋጥመው የመጀመሪያው የምርጫ ክርክር ማክሰኞ ኦሃዮ በምትገኘው ክሊቭላንድ ከተማ ይካሄዳል። ክርክሩ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ፊት ለፊት ቀርበው እንዲያካሂዱ ከታቀደው ሦስት የክርክር መድረኮች የመጀመሪያው ነው።

የዲሞክራትና ሪፖብሊካን ፓርቲ ደጋፊዎች በተቀራራቢ ቁጥር በሚገኙበትና፣ መራጮች ለተፎካካሪዎቹ ያላቸው አመለካከት ከፍተኛ ልዩነት ባሳየበት ኦሃዮ ጨምሮ በጠቅላላ አገሪቱ የሚካሄደው የዘንድሮ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ምርጫ ዘመቻ ማጠቃለያው እየተቃረበ ነው። የክርክሩን ሂደት ለመከታተል ክሊቭላንድ የምትገኘው ዘጋቢያችን ካሮሊን ፕሬሱቲ የላከችውን ዘገባ ይዘናል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply