የመገናኛ ብዙሃን በሀገሪቱ በተፈጠረው ለውጥ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማሳተፍ ረገድ ያላቸው እንቅስቃሴ ዝቅተኛ ነው- የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

Source: https://fanabc.com/2019/02/%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%88%E1%8A%93%E1%8A%9B-%E1%89%A5%E1%8B%99%E1%88%83%E1%8A%95-%E1%89%A0%E1%88%80%E1%8C%88%E1%88%AA%E1%89%B1-%E1%89%A0%E1%89%B0%E1%8D%88%E1%8C%A0%E1%88%A8%E1%8B%8D-%E1%88%88/

አዲስ አበባ፣የካቲት4፣2011 (ኤፍ ቢሲ) በሀገሪቱ በተፈጠረው ለውጥ የብሮድካስት እና የህትመት ውጤቶች የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማሳተፍ የተለያዩ አመለካከቶች እንዲንጸባረቁ እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ ዝቅተኛ መሆኑን አንዳንድ ፖለቲካ ፓርቲዎች ተናግረዋል።

ፋና ብሮድካሰቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የአንዳንድ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በአሁኑ ወቅት በብሮድካስት እና የህትመት የውጤቶች ነጻነት ሀሳብን በማራመድ ረገድ ከዚህ በፊቱ የተሻለ መሆኑ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ለውጡን ተከትሎ አብዛኞቹ የብሮድካስት እና የህትመት የውጤቶች የተለያዩ ሃሳቦችን ከማስተናገድ አንፃር ሰፊ ክፍተት የሚስተዋልባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የወለኔ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብዱላዚዝ የሀገር ውሰጥ መገኛ ብዙሃን ድርጅቶች በአብዛኛው በጥቂት ምሁራኖች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እና መንግስት ላይ ብቻ ትኩረት የሚያደርጉ መሆኑን ተናግረዋል።

የኦሮሞ ብሄራዊ ፓረቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሊበን ዋቆ በበኩላቸው ባለፉት ጥቂት ወራት የመገኛኛ ብዙሃን ሃሳብን በነጻነት ከማስተናገድ አንፃር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን ገልፀዋል ።

ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት የነበረው ባህል በመቀረፍ የሃሳብ ብዝሃነትንና ዴሞክራሲን ከማስተናገድ አንፀር ሰፊ ስራ የሚጠብቃቸው መሆኑን ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ዘርፉ በበለጠ በመንግስት መታገዝ እንዳለበት እና የመገናኛ ብዙሃን ድርጅቶች ህዝበን በቅንነት ለማገልገል ገለልተኛ ታአማኒ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል ።

በአፈወርቅ አለሙ

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.