የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራው የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ ይደረጋል

Source: https://mereja.com/amharic/v2/133229

በአማራ ክልል በሰኔ 15 ዓ.ም ተሞክሮ የከሸፈውና የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች ለህልፈት የዳረገው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የምርመራ ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት ሰሞኑን እያካሄደ ባለው 5ኛ ዙር፤ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አባላትም በሰኔ 15 በተፈጸመው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እና ሌሎች የክልሉ ነባራዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበዋል። የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እንደተናገሩት፤ የክልሉ የጸጥታ ሀይልና ህዝቡ ባደረገው ርብርብ በርካታ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል። በተጠርጣሪዎች ዙሪያ ማስረጃዎች እየተሰባሰበ ነው። የተፈጸመው ወንጀል ከባድና ውስብስብ በመሆኑና ምርመራውም የተለያዩ ዘርፎች ያሉት በአንድ ወር ውስጥ አጣርቶ መጨረስ አልተቻለም ብለው ነገር ግን የምርመራ ውጤቱን በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።
ባለፈው አንድ ወር የሰውና ሳይንሳዊ የቴክኒክ ማስረጃዎችን የማሰባሰብ ተግባር ሲከናወን እንደነበር ያነሱት ኮሚሽነር አበረ፤ ጥቂት ያልተያዙ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።
እንደ አቶ አበረ ማብራሪያ፤ በወንጀሉ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት የልዩ ሀይል አባላት 113ቱ ተለይተው ተለቀዋል። 105ቱ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል የማጣራት ስራው ከተከናወነ በኋላ እየተለቀቁ ሲሆን በሌላ አዳዲስ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር እየዋሉ በመሆናቸው ቁጥሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍና ዝቅ የሚል ነው።
የክልሉ የጸጥታ መዋቅር ከህዝቡ ጋር በመሆን ባደረገው ጥረት ክልሉን ከመፍረስና ህዝቡን ከከፋ ጉዳት መታደግ መቻሉን

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.