የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ

የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ፡፡

የሚቋቋመው ጊዜያዊው የሽግግር መንግስት በወታደሮች ወይንም በሲቪሎች ሊመራ ይችላል ሲሉ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

እዚህ ውሳኔ ላይ የተደረሰው ተቃዋሚዎችና የሲቪክ ማህበራት ለሦስት ቀናት መወያየታቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በውይይታቸው ወቅት ወታደራዊው መንግስት ወደ ቀድሞ ህዝባዊ መንግስት በሚመለስበት ሁኔታ ላይ ነበር የመከሩት፡፡

ከስልጣን የወረዱት ኢብራሂም ቧባካር ኬይታ ለህክምና ወደ ተባበሩት ኤምሬቶች ማምራታቸው ተሰምቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ በወታደራዊው መንግስት የተተኩት ባለፈው ዓመት በነሃሴ መጀመሪያ አካባቢ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በወቅቱም በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውግዘት የቀረረበበት ሲሆን ማሊያውያን ድጋፋቸውን እንደቸሩት ይነገራል፡፡

ማሊ ነጻነትዋን ካገኘች ከ1960ዎቹ ወዲህ የአሁኑ መፈንቅለ መንግስት ለአራተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡

 

ምንጭ፦ቢቢሲ

The post የማሊ ወታደራዊ አመራሮች ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ የአስራስምንት ወራት የሽግግር ጊዜ መንግስት ለማቋቋም ተስማሙ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply