‹‹የማንነት ጥያቄን በግርግር መጠየቅ ተገቢ አይደለም፡፡›› የአማራ ክልል መንግስት

Source: https://mereja.com/amharic/v2/74233

‹‹የማንነት ጥያቄን በግርግር መጠየቅ ተገቢ አይደለም፡፡›› የአማራ ክልል መንግስት

(አብመድ) ሁለቱን ህዝቦች ለማቃቃር የሚንቀሳቀስን ኃይል እንደማይታገስ የአማራ ክልል መንግስት አስታወቀ፡፡
የክልሉ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማኸኝ አስረስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ሰው በመግደል፣ቤት በመዝረፍ እና ንብረትን በማውደም የማንነት ጥያቄ ማቅረብ አግባብ አለመሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ ‹የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ነን ባዮች› የለውጡ አደናቃፊ መሳሪያ መሆን ስለሌለባቸው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡
የቅማንት ህዝብ ጥያቄ ለክልሉ ምክር ቤት ቀርቦ በተገቢው መንገድ ምላሽ እየተሰጠው ባለበት ወቅት ‹የቅማንት የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ነን ባዮች› ለመንግስት ስራ እንቅፋት በመሆን ህዝቡን ወዳልተፈለገ ግጭት እያስገቡት እንደሆነም አስረድተዋል፡፡ የክልሉ መንግስት የህዝቡን የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና ሁለንተናዊ ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ እንዳይመልስ ለውጡን በማይፈልጉ አካላት የመሳሪያ እገዛ ፣ስልጠና እና የገንዘብ ድጋፍ እየተደረገላቸው ህዝቡን ወደ ግጭት እንዲገባ እያደረጉት መሆኑንም ነው የገለጹት፡፡
አሁን ላይም በህዝቡ አስተዋይነት ችግሩ ስር እንዳይሰድ እና የባሰ ቀውስ እንዳይፈጠር ማድረግ ተችሏል ብለዋል አቶ አሰማኸኝ፡፡ መንግስት ችግሩን ለማስቆም እና ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡ የአማራ እና የቅማንት ህዝቦች ለዘመናት አብረው ታሪክ የሰሩ፣ተመሳሳይ ቋንቋ፣ባህል እና ወግ ያላቸው ህዝቦች በመሆናቸው እነዚህን ህዝቦች ለማቃቃር የሚንቀሳቀስን ኃይል የክልሉ መንግስት እንደማይታገስም አስታውቀዋል፡፡

Share this post

One thought on “‹‹የማንነት ጥያቄን በግርግር መጠየቅ ተገቢ አይደለም፡፡›› የአማራ ክልል መንግስት

  1. Worewn tewewna tkklegnawn neger maregaget new selamn miametaw zim bleh womber lay slehonk yametulhn tekebleh …mawrat mefthe ayametam …Tenkek bleh asbeh tenager nege mewuredh aykermna new,,,,,!!!

    Reply

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.