የምህረት አዋጅ የመጠቀሚያ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ ቀረው

Source: https://amharic.ethsat.com/%E1%8B%A8%E1%88%9D%E1%88%85%E1%88%A8%E1%89%B5-%E1%8A%A0%E1%8B%8B%E1%8C%85-%E1%8B%A8%E1%88%98%E1%8C%A0%E1%89%80%E1%88%9A%E1%8B%AB-%E1%8C%8A%E1%8B%9C-%E1%88%B6%E1%88%B5%E1%89%B5-%E1%8B%88%E1%88%AD/

(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 189/2011) መንግስት በቅርቡ ባጸደቀው የምህረት አዋጅ የመጠቀሚያ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ እንደቀረው ተገለጸ።
እስካሁን በዚህ እድል የተጠቀሙና የምህረት ሰርተፍኬት የወሰዱ ሰዎች ቁጥርም 495 ብቻ መሆኑ ታውቋል።
በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና የሚፈለጉ ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውጪ ከሆኑ በኦንላይን በመመዝገብ በወጣው የምህረት አዋጅ መጠቀም እንደሚችሉም ተመልክቷል።
በምሕረት አዋጁ መሰረት በማረሚያ ቤት የሚገኙና ከማረሚያ ቤት ውጭ የሆኑ፣ከግንቦት 30 ጀምሮ የምህረት ሰርተፍኬት እየተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።
እስከ ህዳር 30/2011 ይህው እንደሚቀጥልም ተገልጿል፣በውጭ ሃገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ አቃቤ ሕግ ድረ ገጽ www.Fag.gov.et እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።
በሐገር ክህደት፣በሽብር፣ሕገ መንግስታዊውን ስርአት በሃይል በመናድ፣የጦር መሳሪያ ይዞ ማመጽ በሚል የተከሰሱ ሰዎች በዚህ አዋጅ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተመልክቷል።
በኩብለላ ወንጀል የተከሰሱና የሚፈለጉ ወታደሮች፣በስለላ ወንጀል የተጠረጠሩና የሚፈለጉ ዜጎች፣ የሐሰት ወሬ በማውራት ሕዝብን አነሳስታችኋል በሚል የተከሰሱና የሚፈለጉ ጋዜጠኞችና ሌሎች ዜጎችም በምህረት አዋጁ መሰረት ከክሳቸው ነጻ እንደሚሆኑም ተገልጿል።
በዚህና መሰል ክሶች የተከሰሱና የሚፈለጉ ሁሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በአካል በመቅረብ ወይንም በኦንላይን በማመልከት ከክሳቸው ነጻ መሆናቸው የሚያረጋጝጥ ሰርተፍኬይ ይሰጣቸዋል ተብሏል።
ከግንቦት 30/2010 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነው ይህ አዋጅ የሚቆየው ለሶስት ወር ያህል ማለትም እስከ ህዳር 30/2011 ድረስ እንደሆነም መረዳት ተችሏል።

The post የምህረት አዋጅ የመጠቀሚያ ጊዜ ሶስት ወር ብቻ ቀረው appeared first on ESAT Amharic.

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.