የምርጫ ቅስቀሳ የጀመሩ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ

Source: https://mereja.com/amharic/v2/200977

የምርጫ ቅስቀሳ የጀመሩ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ
በአሁኑ ወቅት የምርጫ ቅስቀሳ የጀመሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ። ቦርዱ ዘንድሮ በሚካሄደው ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበ እየተወያየ ነው።

አሁን ላይ የ’ምረጡኝ’ ቅስቀሳ የጀመሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትክክል አለመሆናቸውን ያሳወቀው ቦርዱ ከቅስቀሳ ዘመቻቸው እንዲቆጠቡም አሳስቧል።የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ቅስቀሳ ሁሉም ፓርቲዎች ቦርዱ ባወጣው የምረጡኝ ዘመቻ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማካሄድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
በመሆኑም አሁን ላይ ቅስቀሳ የጀመሩ ፓርቲዎች ከዚህ እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ መመሪያ አስተላልፈዋል።ይሄን በሚተላለፉ ፓርቲዎች ላይ ቦርዱ አጣርቶ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቀዋል።ቦርዱ ባወጣው ረቂቅ የምርጫ ጊዜ ስሌዳ መሰረት የምረጡኝ ዘመቻ ጊዜ የሚካሄደው ከሚያዚያ 27 እስከ ነሀሴ 5/ 2012 ዓ.ም ነው።
Source – ENA

Share this post

Post Comment

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.