የምድራችን 40 በመቶ የእፅዋት ዝርያዎች ከምድር ገፅ የመጥፋት አዳጋ እንደተጋረጠባቸው አንድ ጥናት አመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ…

የምድራችን 40 በመቶ የእፅዋት ዝርያዎች ከምድር ገፅ የመጥፋት አዳጋ እንደተጋረጠባቸው አንድ ጥናት አመለከተ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የምድራችን አርባ በመቶ የዕፅዋት ዝርያዎች ከምድረ ገፅ የመጥፋት አዳጋ እንደተጋረጠባቸው አንድ ዓለምአቀፍ ጥናት አመልክቷል፡፡ ከአርባ ሁለት ሀገራት የተውጣጡ 200 ሳይንቲስቶች የሰሩትና ለተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበው ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ እፅዋት ለማድሃኒት መስሪያነት፤ ለነዳጅና የምግብ ፍጆታ ለመሸፈን ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳሉ፡፡ ይሁን እንጂ የእፅዋት ዝርያዎች እንዳይጠፉ አስፈላጊ እርምጃዎች ባለመወሰዳቸው የምግብ እጥረትን ለማቅረፍና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል በእጅ ያሉ እድሎች አያመለጡ መሆናቸውን ጥናቱ አመልክቷል፡፡ እኛ አየኖርን ያለነው በርካታ እፅዋቶች ከምድረገፅ እየጠፉበት ባለ ዘመን ነው ብለዋል የጥናት ቡድን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር አሌክሳንድር አንቶኔሊ፡፡ አንደ ጥናቱ ከሆነ ከዓለማችን እጅግ በጣም አነስተኛ ቁጥር ያላቸው እፅዋቶች ብቻ ናቸው የሰው ልጆች ለመድሃኒትና ለኃይል ምንጭነት እየተጠቀሙ ያሉት፡፡ በዓለም ከሚገኙ የዕጽዋት ዝርያዎች ውስጥ ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑት ለሰው ልጆች ለምግብነት መዋል የሚችሉ ቢሆኑም በተጨባጭ የሰው ልጆች እየተጠቀሙ ያሉት ቁጥር ግን አነስኛ መሆኑን በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ እንደጥናቱ ከሆነ ከ2 ሺህ 500 በላይ የኃይል ሰጪ ምግቦች መጠቀም የሚቻል ቢሆንም በዋናነት በቆሎ፣ ስንዴ፤ አኩሪ አተር፣ የወይራ ዘይትን ጨምሮ ስድስት የእፅዋት ዓይነቶችን ናቸው ለኃይል ምንጭነት ጥቅም ላይ እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ እ.ኤ.አ በ2016 ከተገመተው 21 በመቶ በላይ ወደ 40 በመቶ የምድራችን የእፅዋት ዝርያዎች (140 ሺህ የእፅዋት አይነቶች) ከምድረ ገፅ ሊጠፉ ይችላሉ ነው የተባለው፡፡ 723 ለመድሃኒት መስሪያነት የሚያገለግሉ የእፅዋት ዝርያዎች ለመጥፋት አደጋ ከተጋረጠባቸው እፅዋት ዓይነቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ሲል ቢቢሲ ጥናቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply